የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሦስት ስኳር ፋብሪካ ዕሁድ እንደሚመረቅ ተዘገበ

ቦርከና
በሰለሞን ይመር
ጥቅምት 3 ፤ 2011 ዓ.ም

በመጋቢት ወር 2008 ዓ.ም ግንባታዉ የተጀመረዉ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 ስኳር ፋብሪካ እሁድ በይፋ እንደሚመረቅ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በትላንትናዉ ዕለት ዘግቧል፡፡
ከቻይና ልማት ባንክ በተገኘ ከ8 ቢሊዮን ብር በላይ ብድርበካፋና ቤንች ማጂ ዞኖች የተገነባዉ ይህየስኳር ፋብሪካ በቀን በቀን ከ8 ሺህ አስከ 10 ሺህ ኩንታል ስኳር የማምረት አቅም እንዳለው ዘገባ ገልጿል፡፡

በዕለቱም በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የስኳር ፋብሪካዎችን ማስፋፋት ሀገሪቱ የምትከተለሁ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አንዱ አካል ሲሆን የሀገር ዉስጥ የስኳር ፍላጎትን ከማሟላት ባለፈ ለዉጭ ንግድ የሚተርፍ የስኳር ምርት በማምረት የኢኮኖሚእድገትን ለማፋጠን ታስቦ የተጀመረ ፕሮጀክት ነዉ፡፡

ሆኖም ግን የመጀመሪያዉ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ግምገማ ዉጤት እነደ ሚያሳየዉ ከሆነአብዘሀኛወቹ የስኳር ፋብሪካዎ በታቀደላቸዉ የጊዜ ሰሌዳ እየሄዱ እንዳልሆና ዉጤታማ እንዳልነበሩ ተቀምጧል፡፡ ለማሳያ ያክል የጣና በለስ አንድና ሁለት በ2007 ዓ.ም መጠናቀቅ ሲገባቸዉ አልተጠናቀቁም፡፡

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 3 በኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ስር ከሚገነቡት አራት ስኳር ፋብሪካዎች አንዱ ነዉ፡፡ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከመጋቢት 2009 ጀምሮ ወደ ሥራ መግባቱን ዘገባዉ አስታዉሰሷል፡፡

ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.