በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በድብቅ ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 51 ግለሰቦች ተያዙ

Seyfedin Haron
ሰይፈዲን ሃሩን
ፎቶ ፤ ኢዜእ

ቦርከና
ጥቅምት 5 ፤ 2011 ዓ.ም

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕዝብ ላይ ጥፋት ለመፈጸም ወታደራዊ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 51 ግለሰቦችን መያዙን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ማስታወቁን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘገበ።

ኮሚሽነር ሰይፈዲን ሃሩን ዛሬ ለኢዜአ እንዳስታወቁት ግለሰቦቹ የተያዙት ኅብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ የክልሉ ልዩ ኃይል ሰሞኑን በአሶሳ ዞን ባደረገው አሰሳ ነው፡፡
የክልሉ ፖሊስ በአሶሳ ዞን ባደረገዉ አሰሳና ፍተሻ መሰረት በዞኑ ገንገን በተባለ ቀበሌ ጫካ ገብተዉ ስልጠና ሲያካሂዱ የነበሩ 31 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ሲውሉ፣20ዎቹ ደግሞ እጃቸውን መስጠታቸዉን ዘገባዉ ያመላክታል፡፡

ግለሰቦቹ በሥፍራው ከአንድ ወር በላይ ስልጠና ሲከታተሉ እንደነበር አመልክተዉ በስልጠናው ላይ ከነበረው ኃይል የተወሰነው ወደ አጎራባች አገር እንደሸሸም አስታዉቀዉበቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰልጣኞች የ13 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህጻናት ይገኙበታል ሲሉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚስነር ለኢዜአ ተናግረዋል።

“ግለሰቦቹ ይህን ያህል ጊዜ ስልጠና ሲወስዱ የጸጥታ ኃይሉ የት ነበር?” በሚል ተጠይቀዉ ኮሚሽነሩ “የክልሉ መንግሥት ትኩረት በአሶሳና አካባቢው የተከሰተውን የውስጥ የጸጥታ ችግር ማርገብ ላይ መጠመዱ እና አካባቢው መንገድ የሌለውና ጠረፋማ በመሆኑ ለጸረ-ሠላም ኃይሎቹ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ነው” ብለዋል መመለሳቸዉን ዘገባዉ አስነብቧል፡፡

ባሳለፍነዉ መስከረም ወር በክልሉ ተከስቶ በነበር ብሄርን መሰረት ያደረግ ጥቃት ከ 74 በላይ የሰዉ ህይወት ሲጠፋ ከ 90 ሺህ በላይ ዜጎች መሰደዳቸዉን የኢትዮጵያ ሠብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በወሩ መጨረሻ ላይ ያወጣዉ ሪፖርት ያሳያል፡፡

በሰለሞን ይመር
ወቅታዊ እና ሚዛናዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.