ግልጽ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ

በኤድመንተን ካናዳ ከሚኖሩ ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን 

ሃምሌ 12, 2012 ዓ.ም

የህግ የበላይነትን በማስከበር የዜጎችን ህይወትና ንብረት መጠበቅ የመንግስት ቅድሚያ ሃላፊነት ነዉ! በመጀመሪያ፣ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መገደል፣ ከዚያም ተያይዞ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ዘር-ተኮር በሆነ አረመኒያዊ ግድያ ህይወታቸዉን ስላጡት 167 ንጹሃን ኢትዮጵያውያን የተሰማንን ከፍተኛ ሃዘን መግለጽ እንወዳለን። በተጨማሪም በእድሜ ዘመናቸዉ ጥረዉ ግረዉ ያፈሩት ሃብት በእብሪተኛ ቄሮዎች ለወደመባቸዉ ወገኖች፣ ምንም እንኳ ህይወት የማጣትን ያህል ባይሆን፣ በድሃ አገር ለሚኖር ዜጋ የሚያስከትለዉን የኑሮ መቃወስ ስለምንረዳ፣ የተሰማንን ቁጭት ማሳወቅ እንፈልጋለን። ይህን እልቂትና ዉድመት ይበልጥ አሳዛኝ የሚያደርገዉ የዜጎችን ህይወትና ሁለንተናዊ ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነት ያለበት የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ሃላፊዎችና የጸጥታ ሃይሎች ያሳዩት ቸልተኝነት ሲሆን፣ እነዚህ ኃይሎች ከዚህ በፊትም ለነበሩት ዉድመቶችና የሰዉ ህይወት ጥፋት ጭምር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከተጠያቂነት ሊያመልጡ አይችሉም ብለን እናምናለን።

ሙሉውን በፒ ዲ ኤፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published.