ወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር መግለጫና አስቸኳይ ጥሪ

የወሎ ጀግና ወጥር ገመዱን፣ ለነጻነትህ ጥረግ መንገዱን!

ወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማህበር  መግለጫና አስቸኳይ ጥሪ

ከወሎ የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ጥር 23 ቀን 2010 (January 31, 2018) [በፒ ዲ ኤፍ ለማንበብ ይሄንን ይጫኑ] ሕዝብ ቻይ ነው፤ሕዝብ ታጋሽ ነው።ትግስቱ ግን ገደብና መጨረሻ አለው።ትእግስቱን እንደፍርሃት የሚቆጥሩ ጭፍኖችና እብሪተኞች ብቻ ናቸው።የወሎ ሕዝብ እንደተቀረው ወገኑ ላለፉት 27 ዓመታት የወያኔን የግፍ ቀንበር እያንገሸገሸውም ቢሆን ከዛሬ ነገ ወደ ተሻለ አቅጣጫ ሊያመራ ይችል ይሆናል በሚል ግምት ተሸክሞ ኖሯል። […]

የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በአዲስ አበባ በጂምላ እንደታሰሩ ተሰማ

የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በአዲስ አበባ በጂምላ እንደታሰሩ ተሰማ

ቦርከና ጥር 5 2010 ዓም የፋሲል ከነማ እና የመቀሌ ከነማ የእግር ኳስ ጨዋታ በአዲስ አበባ ከተጠናቀቀ በኋላ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በቴድሮስ አደባባይ በሚጨፍሩበት ጊዜ የየፌደራል ፖሊስ ችግር በመፍጠር የፋሲል ከነማን ደጋፊዎችን እንዳሰረ በማህበራዊ ድረ ገጽ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። የፋሲል ከነማ ማሊያ የለበሱ ደጋፊዎችን በጂምላ እንዳሰሩ ነው የተሰማው። የፌደራል ፖሊስ እያሰረ በነበረበትም ወቅት “ወያኔ ሌባ” የሚል […]

በሰሜን ሸዋ የተሰው የነጻነት አርበኞች ማንነት

በሰሜን ሸዋ የተሰው የነጻነት አርበኞች ማንነት

ሚያዚያ 6 2009 ዓ ም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግስት ተቃዋሚዎች በሞት የተቀጡበት ሁኔታ ነበረ። ሆኖም ግን ኢትዮጵያዊም ሆነ ሰብአዊ ክብራቸው በተለይም ህይወታቸው ካለፈ በኋላ የሚገባውን ክብር አይነፈግም ። አሁን ባለው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ መንግስት የፋሺስት ኢጣሊያ ይፈጽመው የነበረው አይነት ኢሰብአዊ ድርጊት በስፋት እየተሰራበት ነው። ባሳለፍነው ሳምንት በሰሜን ሸዋ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የነጻነት […]

ቆሼ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ መጣያ መሬት መንሸራት ከሃያ በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ

ቆሼ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ መጣያ መሬት መንሸራት ከሃያ በላይ ሰዎች ህይወት አለፈ

መጋቢት 3 2009 ዓ ም በአዲስ አበባ ቆሼ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ መጣያ መሬት መንሸራት ምክንያት ቢያንስ ከሃያ በላይ ሰዎች እንደሞቱ ታውቋል። ከጥቂት ሰዓትት በፊት አሶሲየት ፕሬስ የሞቱን ቁጥር 15 በማለት የዘገበ ቢሆንም አሁን በብዙ ሜዲያዎች እየወጣ ባለው ዘገባ የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 24 ሳይደርስ እንዳልቀረ ታውቋል። 37 ያህል ሰዎች በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው ነው። መሬቱ […]

አፈትልኮ የወጣ ልዩ የወያኔ ደህንነት ሪፖርታዥ! የአስቸኳይ ጊዜው አዋጁ እንደሚራዘም ተመክሮበታል!(ሙሉነህ ዮሃንስ)

አፈትልኮ የወጣ ልዩ የወያኔ ደህንነት ሪፖርታዥ! የአስቸኳይ ጊዜው አዋጁ እንደሚራዘም ተመክሮበታል!(ሙሉነህ ዮሃንስ)

ከሙሉነህ ዮሃንስ ጥር 14 ፤ 2009 ዓ ም ወያኔ ከ3 ሳምንት በፊት ከሀገሪቱ በሙሉ ከሚገኙት ዞኖች/ክፍለ ከተሞች በተፅዕኖ ፈጣሪነታቸው ብቻ ሳይሆን በህወሃት ስለት የተገረዘ አእምሮ አላቸው ብሎ የሚመካባቸውን በየዞኑ ከ2-5 ካድሬወች በተለይም አማራና ኦሮሚያ ክልል(የህዝብ አመፅ ከሚበዛባቸው) አካባቢ በርካታ ታማኞችን በ4 ማዕከል(አ.አ፣ መቀሌ፣ ባህርዳርና አዳማ) እስከ 24/05/09 ዓ.ም የሚቆይ ብርቱ ስብሰባ ነው። አንድ ትልቅ ሆቴል […]

ብርቱ ሚስጥር! የጋምቤላ ፍጅት ሲጋለጥ! የጋምቤላ ታጋች ህፃናት ለፖለቲካ ፎጆታ እየሆኑ ነው! (ሙሉነህ ዮሃንስ)

ብርቱ ሚስጥር! የጋምቤላ ፍጅት ሲጋለጥ! የጋምቤላ ታጋች ህፃናት ለፖለቲካ ፎጆታ እየሆኑ ነው! (ሙሉነህ ዮሃንስ)

ሙሉነህ ዮሃንስ ጥር 14 ፤ 2009 ዓ ም ህፃናቶቻቸውን እና እንስሶችን እንደፈለጉ የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት የሚነጥቁባቸው ዞን ውስጥ ከፍተኛ ሹመኛ የሆነ ሰው ነው ያደረሰን። ሚስጥሩ በደረስኩበት መረጃ መረጃ መሠረት ገና ከዚህ በላይ የወረዳው ሰው ሁሉ ሊወሰድ ይችላል ይላል፡፡ ምክንያቶቹን እንዲህ ዘርዝሮ ልኮታል፡- 1. #ለም የእርሻ መሬት ከእኛ እስከ አጎራባች አለ ይህን በሚያርሱ የወያኔ […]

የኤርትራ መሪ ለሃገሮች መሪዎች አቤቱታ ፃፉ (የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ)

የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትናንት የገባውን አዲሱን የአውሮፓ 2017 ዓመተ ምህረት ምክንያት በማድረግ “በኤርትራ ላይ ቀጥሏል” ላሉት የፍትህ መዛባት በደል ዳግመኛ ትኩረት የሚስብ መልዕክት ለብዙ ሃገሮች መሪዎች ልከዋል።

የኤርትራ መሪ ለሃገሮች መሪዎች አቤቱታ ፃፉ (የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ)

የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ታህሳስ 25 ፤ 2006 ዓ ም ዋሺንግተን ዲሲ — ፕሬዚዳንቱ “የሚፈፀመው ኢፍትሃዊ ድርጊት አንድም ምንም ምክንያት ሊሰጠው የማይችል፤ አንድም መሠረታዊ የዓለም አቀፍ ህግጋትና የሞራል ደምቦችን የሚጥስ ነው። ከዚያ በላይ ደግሞ ለክልላዊ ፀጥታና ሰላም አደጋ የሚደቅን ነው” ማለታቸውን ከኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ አትቷል። “የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ኮሚሽን ብይኑን ከሰጠ አሥራ አራት ዓመታት አልፈውም […]

ኢትዮጵያ አስደንጋጭ የዕዳ ክምችት ካለባቸው 10 ሃገራት መካከል አንዷ ናት ተባለ (ኢሳት)

ኢትዮጵያ አስደንጋጭ የዕዳ ክምችት ካለባቸው 10 ሃገራት መካከል አንዷ ናት ተባለ (ኢሳት)

ኢሳት ታህሳስ 19 ፥ 2009 የወጣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አስደንጋጭ ነው የተባለው የውጭ ዕዳ ክምችት ካለባቸው 10 ሃገራት መካከል አንዷ ሆና ተፈረጀች። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ 2015 አም የሃገሪቱ የዕዳ ክምችት ይፋ ያደረገ አንድ አለም አቀፍ መጽሄት የሃገሪቱ የዕዳ ክምችት 22 ቢሊዮን አካባቢ እንደነበር በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት አስፍሯል። ይሁንና በተያዘው የፈረንጆች 2016 አም ይኸው የዕዳ ክምችት ወደ […]

ፋሽስት ወያኔ ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን «በህጋዊ» መንገድ በጠራራ ጸሀይ «በቋሚነት» ወደ ትግራይ እያጓዘ ነው። (አቻምየለህ ታምሩ)

ፋሽስት ወያኔ ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን «በህጋዊ» መንገድ በጠራራ ጸሀይ «በቋሚነት» ወደ ትግራይ እያጓዘ ነው።  (አቻምየለህ ታምሩ)

አቻምየለህ ታምሩ ታህሳስ 19 ፤ 2009 ዓ ም ፋሽስት ወያኔ ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን «በህጋዊ» መንገድ በጠራራ ጸሀይ «በቋሚነት» ወደ ትግራይ እያጓዘ ነው። ከትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በተጻፈ ደብዳቤ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ቅርሳ ቅርሶች ሁሉ ተሰብስብው ወደ ትግራይ እንዲላኩ ትዕዛዝ ተላልፏል። ይህ የመለስ ራዕይ አንዱ አካል ነው። የመለስ ራዕይ ትግራይን በአፍሪካ ቀዳሚ […]

ያልተዘመረለት ጀግንነት! (ሙሉነህ ዮሃንስ)

ያልተዘመረለት ጀግንነት! (ሙሉነህ ዮሃንስ)

በሙሉነህ ዮሃንስ ታህሳስ 12 2009 ዓ ም ወያኔ ከየገጠሩ ወደ ዳባት እስር ቤት ለመክተት የያዟቸውን ብዛት ያላቸው ያልታጠቁ ገበሬወች ሲያጓጉዙ በአካባቢው በጀግንነት የሚታወቁት የጎበዝ አለቆች በጥምረት ድንገተኛ ከበባ ውስጥ አስገብተው ጥቃት በመፈፀም ገበሬወቹን ነፃ አውጥተዋቸዋል። ወያኔወች ተጨንቀዋል ደንግጠዋል። ከተማ እየገባን አመራር ላይ እርምጃ እንወስዳለን የሚል ደብዳቤ ተበትኗል። የጀግኖቹን ተደጋጋሚ አንፀባራቂ ድል ቀኑ ሲደርስ እንገልፀዋለን! አሁን […]