advertisement
ትዕግስት ቱፋ የለንደንን ማራቶን አሸነፈች። እንደ ቢቢሲ ዘገባ የለንደን ማራቶንን ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ ያሸነፈችው ሜሪ ኬይታኒ ውድድሩን ሁለተኛ በመሆን ጨርሳለች።
ትዕግስት ዘጠኝ የሚሆኑ አትሌቶች ጋር ስትፎካከር ከቆየች በኋላ ርቀቱን ለመጨረስ ሶስት ማይል ሲቀር ማርሽ በመቀየር (ቢቢሲ እንዳለው) ወደ ኋላ ጥላቸው ተምዘግዝጋለች።
ወድድሩን በአንደኝነት ከጨረሰች በኋላ ለቢቢሲ ጋዘጠኛ በሰጠችው ቃለ ምልልስ “አይሩ ጥሩ ስላልነበር አስቸጋሮኝ ነበር ፤ ተገፍቸም ነበር። የለንደንን ማራቶን የማሸነፍ ህልም ስለነበረኝ፤ ስለተሳካልኝ በጣም ደስ ብሎኛል” ብላለች።
———
ቦርከና