advertisement
የርቀት ሩጫ ንጉስ ኃይሌ ገብረስላሴ የማንቸስተርን ማራቶን አስራ ስድስተኛ ሆኖ ከጨረሰ በኋላ ራሱን ከውድድር ዓለም አግልሏል።
ዜናው ከተሰማ በኋላ ዓለም ዓቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን ኃይሌ ገብረስላሴ እስከዘለዓለም ድረስ “ንጉሱ” ተብሎ ሊጠራ የሚችልበት ምክንያት ያላቸውን አስር ያህል ነጥቦች በመዘርዘር በድረገጹ ሞቅ ያለ ዜና አስነብቧል።
ለሃያ አምስት ዓመታት በውድድር ዓለም እጂግ የተዋጣለት አትሌት ሆኖ በመቆየቱ ፤ ለሩጫ ባለው የተለየ ፍቅር ፤ የሃያ አምስት የዓለም ሪከርዶች ባለቤት በመሆኑ ፤ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ሜትር እስከ ማራቶን ርቀቶችን በመወዳደር ውጤት እና ክብረወሰን ያስመዘገበ ሁለገብ በመሆኑ ፤ በሚደነቅ አጨራረስ ብቃቱ እና በተደጋጋሚ የኦሎምፒክ ሜዳሊያ ባለቤት በመሆኑ ፤ በቀልድ አዋቂነቱ ፤ በፈገግታው ፤ በዓለም ዓቀፍ መድረክ ባለው መስህብ እና ተጽዕኖ ፤ የተዋጣለት የቢዝነስ ሰው በመሆኑ እና በልበሙሉነቱ የማይረሳ ንጉስ ነው ሲል አሞካሽቶታል።