spot_img
Sunday, May 28, 2023
Homeከሶሻል ሜዲያዜና ትንግርት

ዜና ትንግርት

- Advertisement -

ተፈራ ሥላሴ

ዜና ትንግርት በኢትዮጵያ ቅርብ ቀናት ውስጥ የሚካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ የዜና ዳሰሳ ለማድረግ በመራወጥ ላይ ትገኛለች ። የዜና ትንግርት ምንጮች እንደጠቆሙት ከሆነ የወያኔው ገዢ ስርአት ለምርጫው የሚያደርገውን ዝግጅት አጠናቆ በተጠንቀቅ ላይ ሲገኝ በአንፃሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የበላ ጅብ እንዳልጮኸ ዘግበዋል ።

የወያኔው ሰው በላ ስርአት ለምርጫው ካደረጋቸው ቅድመ ዝግጅቶች መሃከል ዜጎችን በጅምላ መግደልና ማሰር፣ ፓርቲዎችን ማፍረስ፣ የኢሳትን ስርጭት ማስተጉዋጎል፣ የአሜሪካን ባለሥልጣናትን ድጋፍ ማግኘት የመሳሰሉት ይገኙበታል ።ስለተቃዋሚዎች ቅድመ ዝግጅት ከወዲያ ማዶ ከሚሰማው ፉከራና ቀረርቶ በስተቀር ዜና ትንግርት እዚህ ግባ የሚባል መረጃ ስላልነበራት ተስፋ ቆርጣ ነበር።

አሁን ከመሸ ግን ከተቃዋሚዎች አካባቢ የተገኘው ዜና እንዳመለከተው ተቃዋሚዎቹ ገዢውን ፓርቲ ሊያስበረግግና ስፖንሰሮቻቸውንም ሊያስደነግጥ የሚችል ዕቅድ መጠንሰሳቸውን ያበስራል። ዜና ትንግርት ጥቆማው አስቀድሞ ሾልኮ እንዲወጣ በማድረጉዋ ተቃዋሚ ፓርቲዎችንም ሆነ አንባቢያንን ወፍራም ይቅርታ ትጠይቃለች። የዜና ትንግርት አላማ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ማንቀላፋት ብሎም ማንኮራፋት ተስፋ የቆረጠውን ሰፊውን ሕዝብ መታደግ ነው። እነደዚያም ሆኖ አንድ ሁለት ጥቆማዎችን ይፋ ከማውጣት ባሻገር የተቃዋሚዎችን ዕቅድ እንደወረደ የመዘክዘክ አላማ ፈፅሞ የላትም።

ምርጫው ከመካሄዱ ሶስት ቀናት አስቀድሞ የሰላማዊ ትግል አቀንቃኞች ለሕዝቡ ” የጥቁር አብዮትን” ጥሪ ያቀርባሉ ። የጥሪው አጠቃላይ አላማ የወያኔው ስርአት በሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው ለራሱ ለወያኔና ለመላው አለም ቁልጭ አድርጎ ማሳየት ነው።የጥቁር አብዮቱ ጥሪ የምርጫው ዕለት ወንድ፣ ሴት ፣ ወጣት ፣ ሽማግሌ ፣ እስላም ክርስቲያን ሳይለይ አገር ቤትም ሆነ ውጭ ያሉት ኢትዮጵያውያን ከሊቅ አስከ ደቂቅ ጥቁር ለብሰው በመውጣት በስርአቱ ላይ ተቃውሞአቸውን እንዲያሳዩ ይጠይቃል ። ቀኑ የኀዘን ነው። ለምን ቢባል ሰው በላው የወያኔ ስርአት ሕዝቡን በተለያየ መንገድ አስገድዶ ለቀጣዩ አምስት አመታት በባርነት እንዲፈነጭበት የታለመበት እለት ስለሆነ ነው።እንጂማ ጤናማ አእምሮ ያለው ሰው ያስራበውን፣ያስጠማውን፣ያሰረውን፣ያስገደለውን፣ ያሰደደውን፣ የበዘበዘውንና ያስበዘበዘውን ወዘተ ስርአት እንዴት አይኑ እያየ ሊመርጥ ይችላል? ቀኑ በሳዑዲ ፣ በየመን፣ በሊቢያ፣ በየባህሩና በየበረሃው ሕይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያንን የምንዘክርበት ይሆናል ። በዚህ ቀን የሃይማኖት አባቶች እስላሙም ክርስቲያኑም ምህላ እንዲገቡ ይጠየቃሉ ። የአለም ዜና አውታሮች ጥቁር ለብሶ ወደምርጫ ጣቢያ የሚርመሰመሰውን ሕዝብ በመመልከት ስርአቱ ተቀባይነት እንደሌለው ይመሰክራሉ ። ፋሺስቱ የወያኔ ስርአት ሚሊዮኖችን ‘ ለምን ጥቁር ለበሳችሁ?‘ ብሎ ርምጃ ለመውሰድ ብቃቱ አይኖረውም ። ከሞከረም እሰየው! በአጠቃላይ ቀኑ ” የጥቁር አብዮት” ተብሎ ይታወሳል ። ለገዢው ስርአት ቢፍቁት የማይለቅ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያልፋል ።

ዜና ትንግርት ከታጠቁ ተቃዋሚ ኃይሎች ያገኘችው መረጃም ” ይበል” የሚያሰኝ ነው። ታጣቂዎች በኅቡዕ ዋና ዋና የተባሉ የኢትዮጵያ ከተሞች ሰርገው ከገቡ ቆይቷል ። በምርጫው ዕለት የፌዴራል ፖሊስ አባላት ዩኒፎርም በመልበስ ይንቀሳቀሳሉ። እንደአግዓዚ ወታደሮችም ቀይ ኮፍያ አጥልቀው ከገዢው ስርአት አሽከሮች ጋር ይመሳሰላሉ። ከበላይ አካል ትዕዛዝ እስኪመጣ ድረስ አድፍጠው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ። ሕዝቡን ሊከተል ከሚችለው አደጋ ከመከላከል በተጨማሪ ዋና አላማቸው በምርጫው ዕለት በወያኔ ማፊያ ተቋም ስር ያሉ ቢዝነሶችን ከጥቅም ውጭ ማድረግ ነው። ኤፈርትና ሜድሮክ የዚህ ርምጃ ግንባር ቀደም ሰለባዎች ይሆናሉ። አንዳንድ የወያኔ ተላላኪና አቃጣሪ ግለሰቦችም በዚህ ቀን ጭዳ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። የተቃዋሚ ቡድኖች ” ነፃ ግዛት” የሚፈጠርበት እንቅስቃሴም በዚሁ ቀን ይጀመራል ።

ዜና ትንግርት በዛሬው ዕለት ቀንጭባ ያቀረበችው ዘገባ እንደ አንድ የትግል ስልት ሊታይ አንደሚገባ አበክራ ትመክራለች። ዜና ትንግርት እንደቀደምት ዜና አጋሮቿ የሚደርስዋትን ሽሙጥም ሆነ ውስጠ ወይራ መልእክቶች ለአንባቢያን ለማድረስ ወደኋላ አትልም። አላማዋ ጆሮ ያለው እንዲሰማና ጭንቅላቱን እንዲያሰራ መገፋፋት ነው። በዚህ አጋጣሚ ” ዜና ትዝብት ” ሰሞኑን አንዳንድ የሰላማዊ ትግል አቀንቃኞች በታጣቂ ኃይሎች ላይ ስለከፈቱት አላስፈላጊ ዘመቻ የሰላ ሂስ ይዛ ብቅ ልትል እንደምትችል መጠቆም ትወዳለች።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,852FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here