advertisement
የጀርመን ድምጽ ራዲዮ
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ፣ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፤ ባጭሩ መድረክ፣ ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ አዲስ አበባ ውስጥ በጃንሜዳ፤ እጩዎችን የማስተዋወቅና የ«ምረጡኝ» ቅስቀሳ አካሄደ።
የአዲስ አበባው ዘጋቢአችን ፣ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር እንዳለው ፣ በዕለቱ የተጠበቀውን ያህል ሕዝብ ባይገኝም፤ መርሐ ግብሩ ተጠብቆ ሊካሄድ ችሏል። ሕዝቡ፤ በስብሰባው እንዳይገኝ ፣ ፖሊስ ተጽእኞ ማድረጉን ፤ መድረክ አስረድቷል። ዘጋቢችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል።