የኦፌኮ/መድረክ መሪ ተከታታይ ጥቃቶች እንደደረሱባቸው አስታወቁ

የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ዘገባ

አቶ በቀለ ገርባ /የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር/
አቶ በቀለ ገርባ /የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር/

በወለጋ፣ በኢሉባቦርና በጂማ የተለያዩ አካባቢዎች የምርጫ ዘመቻ ሲያካሂድ የነበረ የፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሙድረክ ቡድን ትናንትና ከትናንት በስተያ በአካባቢው የፀጥታ ኃላፊዎችና የገዥው ፓርቲ ደጋፊዎች ባሏቸው ሰዎች ተከታታይ ጥቃቶች እንደተፈፀሙበት የቡድኑ መሪ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ሁኔታውን እያጣሩ መሆናቸውን የተናገሩት የኦሮሚያ ምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር አምባሣደር ዲሳሳ ድርብሳ እስከአሁን “…ችግር ደርሶባቸዋል፤ ይጓዙበት የነበረ መኪና ተሰብሯል፤ ድብደባና ዝርፊያ ደርሶብናል ያሉት እውነት አይደለም ማለት አይቻልም…” ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published.