መታወቂያ የሌላቸው ነዋሪዎች እየመረጡ ነው

ወረዳ 20 ምርጫ ጣቢያ መታወቂያና የምርጫ ካርድ የሌላቸው ነዋሪዎች እየመረጡ ነው ተብሏል፡፡ ነዋሪዎች በዚህ አካባቢ ነዋሪ ከሆኑ ስድስት ወር ሆኗቸዋል በሚል ያለ ቀበሌ መታወቂያ እየመረጡ እንደሆነ ተገልጾአል፡፡ ንፋስ ስልክ ላፍቶ 5ና 8 ምርጫ ጣቢያ ላይ መታወቂያና የምርጫ ካርድ ያልያዙ ነዋሪዎች እየመረጡ እንደሆነ የአካባቢው የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆነው አቶ እስክንድር ጥላሁን ገልጾአል፡፡ በዚሁ ምርጫ ጣቢያ ፖሊስ ምርጫ ጣቢያው ውስጥ እየገባ መረጃ እየወሰደ እንደሆነ ተገልጾአል፡፡ ‹‹ፖሊስ ህግ ከማስከበር ውጭ ምርጫ ጣቢያ ውስጥ ሊገባ አይችልም፡፡ መታወቂያ ስጠይቀው ግን ያሳየኝ የፖሊስ መታወቂያ ነው፡፡ ትክክል እንዳልሆነ ስንነግራቸው ሊሰሙን አልቻሉም፡፡›› ሲሉ ተዘዋዋሪ ታዛቢው ገልጸዋል፡፡

በዚሁ ወረዳ በሌላ ምርጫ ጣቢያ ላይ የተመደቡ ታዛቢም ብዙ መታወቂያችን ጠፍቶብናል ከሚሉት በተጨማሪ መታወቂያ እንደሌላቸው የሚያምኑ ሰዎች እየመረጡ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹እኔ መታወቂያ የሌላቸው መምረጥ እንደሌለባቸው ስከራከር በብሎክ ነው የተሰጠን፡፡ መታወቂያ እንደሌለን እያወቁ በብሎክ ከፍለው ምርጫ ካርድ ሰጥተውናል፡፡ ስለሆነም ቀድመውም ያውቁታል›› በሚል መምረጥ እንዳለባቸው ገልጸውልኛል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ወረዳ 14 ምርጫ ጣቢያ 9 አንድ ግለሰብ ምርጫ ጣቢያው ውስጥ በመግባት ‹‹ንብን ምረጡ›› እያለ መራጩን ሲያስገድድ ተደርሶበታል ተብሏል፡፡

ምንጭ -ነገረ ኢትዮጵያ

Leave a Reply

Your email address will not be published.