advertisement
ሺኑዋ
የዮጋንዳው መከላከያ ሚኒስተር ከተባበሩት መንግስታት የማዕቀብ ኮሚቴ ጋር እንደተወያዮ የቻይናው ሜዲያ ሺኑዋ ዘግቧል። የመከላከያ ሚኒስተሩ ክሪስፕስ ኪዮንጋ ፤ እና የዮኤን 1553 ማዕቀብ ኮሚቴ ሊቀመንበር እና በዮርዳኖስ የተባበሩት መንግስታት ቋሚ ተወካይ ዲና ካዋር ውይይት ያተኮረው በጎረቤት ጎንኮ በሚካሄደው የኮንትሮባንድ ወርቅ ንግድ ዙሪያ ነው።
ችግሩን ለመቅረፍ ዮጋንዳ የምትጫወተውን ሚና ካስታወሱ በኋላ ፤ ኪዮንጋ የዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጂት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ለመርዳት እንዲተባበሩ ጠይቀዋል።