advertisement
የአውሮፓ ህብረት የድንበር ጠባቂ ድርጅት በምህፃሩ ፍሮንቴክስ ዛሬ እንዳስታወቀው፤ ከዓርብ ዕለት አንስቶ ከ5000 በላይ የሜዲትራንያን ባህር ስደተኞችን ለማዳን ተችሏል። ከነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ ከሊቢያ በ25 ጀልባዎች የተጓዙ ስደተኞች ናቸው። የጎርጎሪዮሳዊው አዲስ ዓመት ከገባ ከጥር ወር አንስቶ ብቻ ከ45 000 የሚበልጡ ሕገ ወጥ ስደተኞች ኢጣሊያ ገብተዋል። እንደ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት መረጃ ከሆነ ደግሞ 1,770 የሚሆኑ ወንዶች፣ ሴቶች እና ህፃናት በአደገኛው የባህር ጉዞ ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአውሮፓ ኮሚሽን ቁጥራቸው ከ40 000 በላይ የሆኑ ከሶርያ እና ኤርትራ በኢጣሊያ እና በግሪክ በኩል አውሮፓ የገቡትን ስደተኞች አባል ሃገራቱ እንዲቀበሉ ባለፈው ረቡዕ ጠይቋል።
ምንጭ – የጀርመን ድምጽ ራዲዮ