ደቡብ አፍሪካ የሱዳኑ መሪ ኡመር ሃሰን አልባሽር ደቡብ አፍሪካን ለቀው ስለሄዱበት ሁኔታ አጣራለሁ አለች

ደቡብ አፍሪካ የሱዳኑ መሪ ኡመር ሃሰን አልባሺር በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ደቡብ አፍሪካን ለቀው እንዳይሄዱ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስተላልፎ እያለ ፤ እንዴት ደቡብ አፍሪካን ለቀው እንደሄዱ አጣራለውሁ እንዳለ ሱዳን ትሪቢውን ትላንት በድረ ገጹ ባወጣው ዘገባ አስነብቧል።

ኡመር ሃሰን አልበሽር ደቡብ አፍሪካ የሄዱበት ምክንያት የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመካፈል ሲሆን ፤ ሄግ የሚገኘው ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ኡመር ሃሰን አልበሽር በዳርፉር ሱዳን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ካለቁበት ድርጊት ጋር በተያያዘ በወንጀል እንደሚፈልጋቸው ጠቅሶ፤ ደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ፈራሚ ሃገር እንደመሆኗ ኡመር ሃሰን አልበሽርን በእስር አቆይታ ለዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አሳልፋ እንድትሰጥ ጠይቆ ነበር።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *