- Advertisement -
ፍራንስ24 እንደዘገበው በደቡብ ምስራቅ ፈረንሳይ ሳን ኮንተ ፋቫሊየ በተባለች ከተማ በፋብሪካ ላይ በደረሰ ጥቃት እስካሁን ባለው መረጃ አንድ ሰው ሞቶ በርካቶች መቁሰላቸው ተረጋግጧል። ጥቃቱን ያደረሰው የአሲስ አክራሪ አባል እንደሆነ ራሱን ያሳወቀ ሲሆን ፤ የእስልምና አክራሪ ባንዲራ በቦታው ተገኝቷል።
ጥቃቱ በደረሰበት ቦታ የታረደ የሰው ጭንቅላት እንደተገኘ ፖሊስ አሳውቋል።
ጥቃቱ የደረሰበት ኩባንያ ንብረትነቱ የአሜሪካ ኩባንያ እንደሆነም ታውቋል።
___
ለመወያየት እና እለታዊ ዜናዎችን ለማግኘት ቦርከናን በፌስቡክ ላይክ ያድርጉ። በትዊተርም ለመከታተል ይሄንን ይጫኑ