spot_img
Wednesday, March 29, 2023
Homeዜናየተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እየታደኑ እየታሰሩ ነው

የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እየታደኑ እየታሰሩ ነው

- Advertisement -

ነገረ ኢትዮጵያ
ከታሳሪዎቹ መካከል ሁለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ናቸው

በአማራ ክልል የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በአዲስ መልክ እየታደኑ እየታሰሩ መሆኑን የአይን እማኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በምዕራብ ጎጃም ዞን ወንበርማ ወረዳ ከትናንት ሰኔ 18/2007 ዓ.ም ጀምሮ የሰማያዊ፣ የቀድሞው አንድነትና የመኢአድ አመራሮች እየታደኑ እየታሰሩ መሆኑ ታውቋል፡፡ ትናንት ሰኔ 18/2007 ዓ.ም የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው አዳነ አለሙ እና የመኢአድ አመራር የነበረው አቶ አበባው የተባለ ግለሰብ በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ ዛሬ ሰኔ 19/2007 ዓ.ም በወንበርማ ወረዳ ሸንዲ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ የተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የነበረው አቶ ፈንታሁን ብዙአየሁ እና አንድ የቀድሞው አንድነት አመራር መታሰራቸው ታውቋል፡፡

ሁለቱም የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ያለ አግባብ በዕጩነት ተሰርዘናል በሚል ክስ መስርተው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረዛቸው አግባብ አለመሆኑን ወስኖ ወደ ዕጩነት ሲመልሳቸው የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎት ከዕጩነት እንዲሰረዙ አድርጓል፡፡ አቶ ፈንታሁን ብዙአየሁ እና አዳነ አለሙ እነሱን ጨምሮ ሌሎች የተሰረዙ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ወደ ዕጩነት እንዲመለሱ ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ተገልጾአል፡፡

በተጨማሪም በምስራቅ ጎጃም ዞን የቀድሞ አንድነት አስተባባሪ የነበሩት አቶ ልዑልሰገድ እምባቆም በደብረማርቆስ ከተማ ፖሊስ መያዛቸው ታውቋል፡፡ አቶ ልዑልሰገድን ዛሬ ሰኔ 19/2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ የያዛቸው የደብረማርቆስ ፖሊስ እስከ ቀኑ 5 ሰዓት ደብረማርቆስ ከተማ ውስጥ ካሰራቸው በኋላ ‹‹የያዝነህ እኛ አይደለንም፡፡ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ይፈልግሃል!›› በሚል ወደ ባህርዳር ከተማ ወስዷቸዋል ተብሏል፡፡

በየ አካባቢው በፖሊስ የተያዙት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ለጥቂት ጊዜ በየአካባቢያቸው እስር ቤቶች ከቆዩ በኋላ ወደ ባህርዳር ከተማ መዛወራቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በጥቅምት ወር 2007 ዓ.ም መጀመሪያ የሰማያዊ፣ የአንድነትና የመኢአድ አመራሮችና አባላት ከየ ክፍለ ሀገሩ ተይዘው መታሰራቸው ይታወቃል፡፡

___
ለመወያየት እና እለታዊ ዜናዎችን ለማግኘት ቦርከናን በፌስቡክ ላይክ ያድርጉ። በትዊተርም ለመከታተል ይሄንን ይጫኑ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,460FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here