advertisement
የአየር ላይንዱ አይሪሽ ኢንዲፔንደንት እንደዘገበው ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዳብሊን አይርላንድ በኩል ወደ ሎሳንጀለስ በጀመረው አዲስ በረራ ላይ የነበሩ ሰባት ያህል ተሳፋሪዎች ዳብሊን አይርላንድ እንደደረሱ ጥገኝነት ጠይቀዋል።
ጥገኝነት ከጠየቁት ውስጥ ሁለቱ ህጻናት እንደሆኑ ከአይሪሽ ኢንዲፔንደንት ዘገባ ማወቅ ተችሏል።
መንገዶኞቹ ዳብሊን አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ ሰተት ብለው ወደ ኢሚግሬሽን ቢሮ በመሄድ ጥገኝነት ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ ሁሉም መንገደኞች ከአዲስ አበባ ሲነሱ ህጋዊ የጉዞ ሰነድ የነበራቸው እንደሆነ እንዳረጋገጠ በቃል አቀባዮ በኩል አስታውቋል።