- Advertisement -
ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ መንግስት በሸብርተኝነት ከሷት ረዥም አመት ቢፈርድባትም ከአራት አመት በላይ የእስር ቆይታ በኋላ ዛሬ በድንገት ተጠርታ ከእስር ተለቃለች።
በሃገር ቤት በእንግሊዝኛ የሚታተም የአዲስ ስታንዳርድ ጋዜጣ እንዳስነበበውም ፤ ስድስት ያህል ተማሪ የኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን በተመሳሳይ ሁኔታ ከእስር እንደተፈቱ ለማወቅ ተችሏል።
ሆኖም ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን እስካሁን በእስር ላይ ናቸው።
ተጨማሪ እስረኞች ይለቀቃሉ የሚል ግምት ቢኖርም ፤ በእርግጠኝነት እነማን እንደሚፈቱ የታወቀ ነገር የለም። የኢትዮጵያውያን ሙስሊም አፈላላጊ ኮሚቴዎች ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፤ እስክንድር ነጋ ፤ እና ተቃዋሚ ፓለቲከኞች ከታሳሪዎች ይገኙበታል።