
ፎቶው ከ EBC ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ነው
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ዛሬ የሶስት ቀን የስራ ጉብኝት ለማድረግ ከጥቂት ሰዓታት በፊት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ኦባማ ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት ኬኒያ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት ካጠናቀቁ በኋላ ነው። በኬኒያ ሊያስተጋቡ ይዘውት የነበረው የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ( ግብረ ሰዶም) በኬኒያው ፕሬዝዳንት ተቀባይነት ሳያገኝ ፤ ፕሬዝዳንቱ ትብብራቸው በልማት እና በኢኮኖሚ ጉዳይ ላይ ብቻ እንዲያተኩር እንደሚፈልጉ በግልጽ ተናግረዋል። በኬኒያ የእምነት ተቋማት የግብረ ሰዶምን አጀንዳ በጽኑ ተቃውመውታል።
በኢትዮጵያ በሚያደርጉት የስራ ጉብኝት ኦባማ በሁለትዮሽ እና በጸጥታ ጉዳዮች እንደሚመክሩ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ቢያስታውቅም ፤ ታዛቢዎች የግብረ ሰዶምም አጀንዳ እንደሚነሳ ይገምታሉ።
ባራክ ኦባማ አዲስ አበባ ሲገቡ ፤ በአዲስ አበባ ሰማይ የማርያም መቀነት ታይቷል። ግብረሰዶማውያኑ የሚጠቀሙበት ባንዲራ በማርያም መቀነት ካሉ ቀለማት ጋር የሚመሳሰሉ ናቸው።
ቴዎድሮስ አድሃኖም የተዝጎረጎረ ዣንጥላ ይዘው ለመቀበል በቦሌ ተገኝተዋል።
ኦባማ ከመምጣታቸው ከጥቂት ሳምንታት በፊት ሪዮት አለሙን ጨምሮ የተወሰኑ ብሎገሮች እና ጋዜጠኞች ከእስር ቢለቀቁም ፤ አሁንም በርካታ ብሎገሮች እና ጋዜጠኞች በእስር ላይ ይገኛሉ።