የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናተንያሁ ኢትዮጵያን ጎበኙ

ሐምሌ  1 ፤Natenyahu and Hailemariam Desalegne - source The Prime Minister Of Israel page on Facebook  2008 ዓ ም

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንጃሚን ናተንያሁ በአፍሪካ ሀገሮች ያደረጉትን ጉብኝት ለማጠናቀቅ ትላንት ኢትዮጵያ ገብተዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ከፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ጋር ተወያይተዋል። ውይይታቸው ንግድን እና የሁለትዮሽ ግንኙነትን የሚመለከት እንደነበር ታውቋል።

እስራኤል በማዕድን ዘርፍ ከ አንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በኢትዮጵያ ኢንቬት አድርጋለች።

ከንግድ በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን ይሁዴዎች ወደ እስራኤል ሀገር ስለሚሄዱበት  ሁኔታ እንደተነጋገሩ እና ናታንያሁ በቅርቡ የማጓጓዙ ስራ እንደሚጀመር ተናግረዋል።

እስራኤል በአፍሪካ ህብረት የታዛቢነት ቦታ እንዲኖራትም ኢትዮጵያ ድጋፍ እንድታሳይ ተጠይቋል። ኃይለማርያም ዘመቻውን እንደሚደግፉት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስተር የፌስ ቡክ ገጽ ላይ የወጣው ዜና ይጠቁማል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.