advertisement
ሐምሌ 24 2008 ዓ.ም
ከማስተዋል ፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ
የጎንደር ሕዝብ እምብይ ብሎ በድፍረት ለተቃዉሞ ወጣ እንጅ ገዥወች እስከ መጨረሻዋ ስዓት ድረስ ህዝቡ ለሰልፍ እንዳይወጣ ሲያስጠነቅቁ እና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር አሰማርተው ሲያስፈራሩ ነበር:: ባለፈው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ለመያዝ ሲሞክሩ ያጋጠማቸው የአፀፋ ምት ትልቅ ትምህርት ሁኗቸው ዛሬ ላይ ሌላ ደም መፋሰስ እንዳይኖር ልቦና ማግኘታቸው መልካም ጅምር ነው:: የጎንደር ሕዝብ ራሱን በራሱ ነው ያስከበረው:: እንደ ህወሓት አይነቱን ገዳይ እንዳይገድልህ ማድረግ የምትችለው በገደለ ቁጥር እሱም እንዲሞት ስታደርገው ብቻ ነው:: ባዶ እጅህን ሁነህ ከታጠቀ ሽፍታ ጋር መከባበር ብሎ ነገር የለም:: ጥያቄህ መልስ የሚያገኘው ፣ ብትናገር የምትሰማው፣ ምን አባቱ ያመጣል ተብለህ የማትናቀው፣ የማትገደለው መገዳደር የሚያስችል አቅም ስትገነባ ብቻ ነው:: ደካማ ከሆንክ ምንም ሰላማዊ እና ጨዋ ብትሆንም ጉልበተኞች ጥጋብ አላስችላቸው ሲል ሰላምህን ይነሱሃል፣ በሰላም እንድትኖር ለጦርነት ተዘጋጅ ያለው ማን ነበር?
አገራችን ጎንደር ወንዛችን ተከዜ
ማን ይናገረናል እምብይ ያልን ጊዜ