advertisement
ሐምሌ 24 2008 ዓ.ም
ዛሬ በምስራቅ ሃረርጌ በአወዳይ ከተማ በተነሳ ህዝባዊ አመጽ ቢያንስ ስድስትሰዎች ተገድለው ሃያ አምስት ያህል ቆስለዋል እንደ ኦሮሚያ ሜዲያ ኔትዎርክ ዘገባ።
በአወዳይ የህዝባዊ አመጽ እንደተነሳ ፤ ሰባት መኪና ያህል የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አጋዚ ጦር ወደ ከተማዋ በመግባት ፤ ፓሊሶችን እና የአካባቢውን ሚሊሻ ትጥቅ በማስፈታ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን እያሰሙ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ አረመኔያዊ እልቂት ፈጽሟል።
ባለፉት ጥቂት ወራት በተነሳው የኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ሕዝባዊ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ቢያንስ 400 ያህል ሰላማዊ ዜጎች መገደላቸው ይታወሳል።
ዛሬ በአወዳይ የተነሳው ተቃውሞ በጎንደር ታላቅ ሰልፍ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው።