advertisement
ሐምሌ 25 2008 ዓ.ም
ሸበሌ ዜና
በሶማሊያ የህገ መንግስት እና መግባባት ተጠባባቂ ሚኒስትር የሆኑት ኦስማን መሃመድ አሊ የኢትዮጵያ ልዮ ኃይል በማዕከላዊ ሶማሊያ የወንጀል ድርጊት ፈጽሟል ሲሉ የኢትዮጵያን መንግስት ከሰሱ።
ሚኒስትሩ ለሸበሌ ራዲዮ በስልክ እንደገለጹት የልዮ ኃይል አባላት ሙዱግ በሚባለው የማዕከላዊ ሶማልያ ያሉ በርካታ ትንንሽ ከተሞችን በመውረር ያልታጠቁ ሲቪሊያኖች ላይ ጥቃት በማድረስ ቤቶቻቸውን አቃጥለዋል።
በታንክ እና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎች አካባቢዮን የወረረው የልዮ ኃይል ሰራዊት በሙዱግ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ አስገድደዋቸዋል ሲል የሸበሌ ዜና ጨምሮ ገልጿል።
———
ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ ፤ ሼር ያድርጉ