spot_img
Thursday, November 30, 2023
Homeመጽሐፍትአባቴ እና እምነቱ (በስምረት አያሌው ታምሩ)

አባቴ እና እምነቱ (በስምረት አያሌው ታምሩ)

advertisement

ስምረት አያሌው ታምሩ “አባቴ እና እምነቱ” በሚል ርዕስ የጻፈችው መጽሃፍ ከታተመ ሰንብቷል። ግሩም መጽሃፍ!

ከአለቃ አያሌው ታምሩ የስጋ ልጂነትም ባለፈ ( እሷም በግጥሟ ብላለች) የመንፈስ ልጃቸውም እንደመሆኗ የአባቷን እምነት ልቅም አርጋ ይዛ በጥልቀት እና በስፋት በግሩም አማርኛ ማስተላለፏ ብዙ ላይደነቅ ይችል ይሆናል፤ በሌላ አንጻር ግን እሷ ሆና ተገኝታ ነው እንጂ “ልጂ እንደአባቱ አይሆንም” የሚባልም ነገር ስላለ ምስጋና ይገባታል
ከአለቃ አያሌው ታምሩ ታሪክ እና አስተዋጽኦ ሌላ ፤ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተነሱ ችግሮችን፤ በኢትዮጵያ ላይ ያንዣበበውን አደጋ በየዕለቱ የምናየውን ውጤት ሳይሆን ምንጩን ጠቁመዋል። በዚያ ረገድ መጽሃፉን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች ብቻ ሳይሆን የሌላ እምነት ተከታዮችም ማንበብ ያለባቸው መስሎ ይሰማኛል።

እሳቸው ገና አዲስ አበባ ሲመጡ ( ከሃምሳዎቹ በፊት መሆኑ ነው) የነበረውን ወጣት ለማንነቱ እና ለሃገሩ ታሪክ ግድ የለውም ያሉትን ነገር ሳስብ ስለአሁኑ ዘመን ወጣት በዚያው አንጻር ምን ሊሉ እንደሚችሉ ማሰብ ይከብዳል!

ስለ ሃበሻ ፈረንጆች ፤ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያንን ህልውና ከውስጥ ለማጥፋት እና ሮማዊ ለማድከረግ ስለተሞከረው ነገር እና እሳቸው ነገሩን ለመዋጋንት ብቻቸውን በሚያስብል ሁኔታ ያደረጉት ነገር ግሩም ነው! አለቃ አያሌው ያሉት ብዙ ቁም ነገር እያለ ፤ ብዙው ግን እንዳልተሰማ እንዳልታየ እየተደናቆረ ታልፏል። ለምሳሌ “ካቴድራል” የሚባል ስያሜ ኢትዮጵያዊ አይደለም ለምን መዋስ አስፈለገ “መንበረ ጸባኦት” የሚል የእግዚያብሔርን አሸናፊነት የሚገልጽ ስም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እያላት የሚለውን ማንም መመለስ አልፈለገም። ዛሬም ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይባላል! ማህበረ ቅዱሳን ራሱ በዚህ አንጻር ምን እንደሰራ ወይ እየሰራ እንደሆነ አላውቅም!
በባዶ ሜዳ ስንቆለል ሌላ ያመለጠን ትልቅ በረከት የግዕዝ ቋንቋ አለመቻላችን እንደሆነ እንደገና አሳስቦኛል መጽሃፉ። ከሃይማኖትም ውጭ ቀደም ካሉ ኢትዮጵያው አስተሳሰቦች ጋር መስተጋብር እንድናደርግ ይረዳን ነበር። ለምሳሌ ስለዮሃንስ አፈወርቅ አንዳንዶቻን የሰማን ቢሆንም የማንበብ እድሉ የደረሳቸው በጣም በቁጥር የተወሰኑ እንደሆኑ መገመት አይከብድም።

“የደብተራ ታሪክ” እያልን ካንጓጠጥናቸው ብዙ ስራዎች ለመሆኑ ምን ያህሉን በጥሞና አንብበናል ፤ ጥያቄ ነው ለኔ። ራሳችንን ሳናነብ ፤ የኢትዮጵያን ጣዕም ሳይገባን እኮ ነው ኢትዮጵያን በውጭ መነጽር ማየት አይተን ወደ ትችት እና ወደ ፈጠራ ታሪክ የገባነው! ውጤቱ ምን ሆነ? የምናውቀው ነው።

የስምረት አያሌው መጽሃፍ እጂግ በጣም ግሩም ነው፤ የትም ፈልጋችሁ ብታነቡ እንደምትደሰቱበት እርግጠኛ ነኝ። ምክንያት የአያሌው ታምሩን ታሪክ እና ስራ ሳይሆን የምታዮበት ራሳችሁንም ለማየት ጥሩ መነጽር ነው።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here