- Advertisement -
ሐምሌ 25 2008 ዓ.ም
ኗሪነታቸው በሳንፍራንሲስኮ የሆነው ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ “የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ” በሚል ርዕስ የጻፉት መጽሃፍ ለህትመት መብቃቱን እና በኢትዮጵያ ፤ በአውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ በስርጭት ላይ መሆኑን ያበሰሩት ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ወር ማብቂያ አካባቢ ነው።
ከርዕሱ ብቻ በሚመስል ሁኔታ መጽሃፉ በማህበራዊ ድረ ገጽ ብዙ ውዝግብ እና ንትርክ አስነስቷል።
እንደዶክተር ፍቅሬ ገለጻ መጽሃፉ በምርምር ላይ የተመሰረተ ነው።
ከመጽሃፉ የጀርባ ሽፋን ባለው መረጃ በመመስረት መጽሃፉ ኢትዮጵያን ላለፉት 700 ዓመታት የገዛው ማን ነው ፤ አማራ ወይንስ ኦሮሞ?ባለፉት ስርወ መንግስታት የአማሮች ተሳትፎ ምን ያህል እና እስከምን ድረስ ነበር? የሚሉትን ጥያቄዎች ከመሰንዘር በተጨማሪ ኦሮሞ የመጣው ከማዳጋስጋር ነው የሚለውን አስተሳሰብ የሚያጣጥል ይመስላል።
——————————
በመጽሃፉ ላይ አስተያየትም ሆነ እይታ ማቅረብ የሚፈልግ ሰው ካለ ለድረ ገጺ አዘጋጂ በ editor@borkena.com መላክ ይቻላል።