ከሰዓታት በፊት በጎንደር በተነሳ አመጽ ቢያንስ አንድ ሰው ተገድሏል ፤ ጎንደር ቀውጢ የጦርነት ቀጠና እንደመሰለች ይነገራል

ሐምሌ 29 ፤ 2008

በማህበራዊ ድረ ገጽ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ዛሬ በጎንደር ድንተገኛ ተቃውሞ ተነስቷል። ቢያንስ አምስት ሺህ የሚገመቱ ሰልፈኖች የጎንደር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት በመሆን ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።

ሰልፉ ፍርድ ቤት የሆነነት ምክንያት የወልቃይት ጥያዊ ኮሚቴ አባል እና አመራር የነበሩት ኮሎሌል ዘውዱ ፍርድ ቤት ቀርበዋል የሚል ዜና በጎንደር ከተሰማ በኋላ ነው። ኮሎኔሉን አሁን ከሚገኝበት የጎንደር አንገርብ እስር ቤት ወደ ማዕከላዊ ለማዛወር የጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች 4 ለ 1 የሆነ ድምጽ እንዳሳለፉ የተሰማው ባለፈው ሳምንት ነው። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እስካሁን በይፋ ክስ ያልተመሰረተበት ሲሆን ፤ ክስ ቢመሰረትበት እንኳን ጉዳዮ በጎንደር ፍርድ ቤት ደረጃ ሊታይ የሚችል ሲሆን ወደ ማዕከላዊ ማዛወሩ አግባብነት ያለው አካሄድ አይደለም በማለት የህግ ሰዎች አስተያየት ይሰጣሉ።

የኢሳት ሰበር ዜና ዘገባ ቪዲዮ እንደሚያመለክተው መጀመሪያ ሰልፈኞቹ ላይ አስለቃሽ ጭስ የተተኮሰ ቢሆንም ፤ ወዲያውኑ በሰልፈኞቹ ላይ የጥይት ተኩስ ሩምታ ተከፍቷል።

በማህበራዊ ድረ ገጽ የተለቀቀ ፎቶ እንደሚያሳየው አንድ ወጣት እጂግ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደለ ያሳያል። ሆኖም የጎንደር ወጣት ባለማፈግፈግ ትግሉ መንፈሰ ጠንካራነት የተሞላበት እንደሆነ አስመስክሯል።

ጎንደር ሙሉ ለሙሉ ወደ ጦርነት ቀጣና እንደተቀየረች ባለፉት ሰላሳ ደቂቃዎች በማህበራዊ ድረገጽ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፤ ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የጎንደር ወጣት ተገድሏል።

Gondar protest now

ፎቶ ምንጭ : ሶሻል ሚዲያ

Leave a Reply

Your email address will not be published.