ነሃሴ 1 2008 ዓ ም
በርካታ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች በባህር ዳር ጎዳናዎች ዛሬ ጧት ለተቃውሞ ስልፍ ተመዋል ። ተቃውሞው ቀደም ብሎ ዝግጂት የተደረገበት ሲሆን ፤ ሰልፈኞቹ ወደ ትግራይ ክልላዊ መንግስት የተካለለው የወልቃይት የማንነት ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ጥያቄ አቅርበዋል። አሁን በስልጣን ላይ ያለው መንግስ ወልቃይትን በኃይል ርምጃ ወደ ትግራይ ከማካለሉ በፊት ወልቃይት ለብዙ መቶ አመታት የጎንደር አካል እንደነበረ ይታወቃል።
ሰላማዊ ተቃውሞው “ኢትዮጵያዊነትን መጠየው አሸባሪነት አይደለም” ፤ “ሁላችንም ኮሎኔል ዘውዱ ነን” “አንዳርጋቸው ጽጌ መሪያችን እንጂ አሸባሪ አይደለም” “በቀለ ገርባ አሸባሪ አይደለም” የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን እንዳሰሙ ከኢሳት ዘገባ ለማወቅ ተችሏል።
ሰልፈኞቹ ዙሪያ ጥምጥም ሳይሄዱ የግፍ አገዛዝ ያሉትን የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እንዲያከትም ጠይቀዋል። በተጨማሪም በጎንደር ፤ በሃረር ፤ በወለጋ ፤ በባሌ በናዝሬት እና ሌሎች ቦታዎች የተደረጉ ሰልፎችን እና የተነሱ ጥያቄዎችን ደግፏል።
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ አጋዚ በመባል የሚታወቁት የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ታማኝ ወታደሮች የተኩስ ሩምታ እንደከፈቱ እና ወደ ሰልፈኞቹ እንደተኮሱም መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሆኖም በሰው ህይወት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን በዚህ ሰዓት አልታወቀም።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የፓለቲካ ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እየመጣ ነው። የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከፍተኛ የጦር ጄኔራል በመሆን የሰሩ እንደ ጻድቃን ገብረተንሳይ እና አበበ ተክለኃይማኖት ያሉ በስልጣን ላይ ያለው ቡድን የፓለቲካ አያያዝ ሃገር ሃገሪቱን ወደማትወጣበት ውጥንቅጥ ውስጥ እያስገባት እንደሆነ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል አሁን በስልጣን ላይ ያለው ቡድን በመዋቅር ደረጃ ያስፋፋው የጎሳ ፖለቲካ የከፋ አቅጣጫ እንዳይዝ ስጋታቸውን የሚገልጹ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ብዙ ነው። ትላንትና አጋዚ በወሰደው የኃይል ርምጃ በጎንደር እና በኦሮሚያ የተለያዮ ከተሞች ቢያንስ አስር ሰዎች እንደተገደሉ ይነገራል።
በጎንደር እና አሁን በጎጃም የወልቃይትን ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ የወጣው ህዝብ ላይ የተኩስ ሩምታ እንዲከፈት ያዘዘው መንግስት ፤ በትግራይ ስለ ወልቃይት የሚደረገውን ተቃውሞ የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ እያዘጋጀም እንደሆነ ይነገራል።
______
ካነበቡ በኋላ ሼር በማድረግ ይተባበሩ ፤ በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉን