ነሃሴ 1 2008 ዓ ም
ትላንት በባህር ዳር እየተደረገ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ አጋዚ በመባል የሚታወቁት የህወሓት ታማኝ ወታደሮች በሰላማዊ ሰዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ ሰላሳ ሰባት ሰዎች ሲገደሉ ፤ ሃምሳ ያህል ቆስለዋል።
ሆኖም ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። ትላንት ለተገደሉት የከተማዋ ነዋሪዎች የቀብር ስነ ስርዓት ከተደረገ በኋላ ለቀስተኛው ወደ ህዝባዊ እምቢተኝነት ተመልሶ ድምጹን ሲያሰማ ውሏል።
ሱቆች እና የመንግስት መስሪያቤቶ የተዘጉ ሲሆን፤ የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎትም እንደተቋረጠ ለማወቅ ተችሏል። ዛሬ በተደረገውም ሰልፍ ላይ የመንግስት ታማኝ ወታደሮች የተኩስ ሩምታ የከፈቱ ሲሆን፤ የደረሰውን የጉዳት መጠን እንካሁን ማረጋገጥ አልተቻለም።
በተመሳሳይ ሁኔታ በባሌ ፤ በሃረር ፤ በአርሲ ፤ በወለጋ እና ከፊል ሸዋ የኢትዮጵያ ክፍሎች የኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ከቅዳሜ ጀምሮ ብቻ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ከአርባ በላይ የሚገመቱ ሰላማዊ ዜጎች እንደተገደሉ ታውቋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ በባህር ዳር እና ጎንደር ፤ በደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ምዕራብ እንዲሁም በመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል በሃረር፤ በባሌ ፤ በአርሲ እና ወለጋ የተነሱት የተቃውሞ ሰልፎች የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የግፍ አገዛዝ እንዲያከትም ጠይቀዋል።
በውጭ የሚገኙ የተለያዮ ሚዲያዎች ህዝባዊ ተቃውሞን የዘገቡ ቢሆንም የብዙዎቹ ዘገባ የሟቾች የቁጥር መዛባት እና ሌሎችም መሰረታዊ ችግሮች ያሉበት እንደሆነ ይስተዋላል። እንደፋይናንሺያል ታይምስ ያሉት ለምሳሌ በዘገባው ውስጥ “የአፍሪካ ምርጥ ምርታማ ኢኮኖሚ የፖለቲካ አለመረጋጋት አደጋ ተደቅኖበታል” ሲል ዘግቧል።
በእንደ እውነቱ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ባለፉት 25 ዓመታት ትርጉባ ባለው “ፖለቲካዊ መረጋጋት” ኖሯል ለማለት አይቻልም።
_____
ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ። ካነበቡ በኋላ ሼር ማድረግ አይርሱ