spot_img
Wednesday, November 29, 2023
Homeነፃ አስተያየትይድረስ «Status Quo»ው ብቻ ለሚመቻችሁ ወዳጆቼ

ይድረስ «Status Quo»ው ብቻ ለሚመቻችሁ ወዳጆቼ

advertisement

ኤፍሬም እሸቴ አደባባይ ላይ እንደጻፈው
ነሃሴ 5 2008 ዓ.ም

Status Quo የሚለውን ቃል በአንዲት ቃል እስር፣ ትርጉም አድርጌ ባቀርባት ደስ ባለኝ። ርዕሴንም በአማርኛ አድርጌው አርፍ ነበር። ግን አስቸጋሪ ስለሆነ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት አማከርኩ። እንዲህ ተርጉሞታል። Status Quo: the current situation; the way things are now» (Source: Merriam-Webster’s Learner’s Dictionary) በቀላሉ ስንተረጉመው «አሁን ያሉት ነገሮች እንዳሉ፣ ሳይለወጡ» (የነበረው እንዳለ ወይም ‘ዘሀሎ’ እንበለው የግእዙን ወስደን?) እንደማለት ነው። ነገሮች/ things የተባሉት ደግሞ «social or political issues. ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች» መሆናቸውን አክሉበት።

በዚህ በሰሞኑ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ስታትስኮው ሊለወጥ እንደሚችል የተረዱ ነገር ግን የዚህን ለውጥ ነገር በእጅጉ የፈሩ ብዙ ሰዎችን ተመልክተናል። መግለጫ በመግለጫ ካደረጉን ፓትርያርክ ማትያስና የበታቾቻው እንዲሁም የሙስሊም መሪዎች እና ሌሎች ቤተ እምነቶች በተጨማሪ ሌሎች ወገኖችም የየአቅማቸውን ጥብቅና ለስታትስኮው በመቆም ላይ ናቸው።

አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ለነማን እንደተመቸ፣ እነማን ተደስተው እንደሚኖሩ፣ እነማን እንደተቸገሩ ፍንትው ብሎ እየታየ ነው። አሁን ላለው ነባራዊ ሁኔታ መቀጠል ጥብቅና የሚቆሙት ሰዎች ሐሳባቸውን የሚያቀርቡት «ለውጥ ቢመጣ ጥቅማችን ይነካል» በሚል ደረቅ ስብከት ሳይሆን «ልማታችን እንዳይደናቀፍ» (ጌታቸው ረዳ)፤ «የሕዝቡ ንብረትና ሀብት እንዳይጎዳ/አሁን ተከሥቶ ያለው ውዝግብና ተሐውኮ ቆሞ ችግሮች ሁሉ በሕጋዊ መንገድ፣ በወንድማማችነት መንፈስና በውይይት ይፈቱ» (ፓትርያርክ ማትያስና መሰሎቻቸው)፤ «ምናለበት ግን ዘረኝነቱን ትተን በፍቅር ብንኖር። ሰዉም በሥነሥርዓት ጥያቄውን ለሚመለከተው አካል ቢያቀርብ» (የዋህ መሳይ ፌስቡከሮች) እያሉ ነው። የሚከተሉት ወዳጆቼ ጥያቄም ከላይ ካነሳኋቸው ሰዎች አስተያየት የሚደመር ነው።

ጥያቄ ከወዳጆቼ፡- «አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሕዝብና የመንግሥት ችግር ሊገባኝ አልቻለም። በጣም ያሳዝናል። ምናለበት ግን ነገር ብታበርዱ? ይሄ ግርግር ለማንም አይጠቅምም። ሁሉም ነገር በሰላም ቢሆን አይሻልም? እኔ ምኑም አልገባኝም በእውነት።»

እኔም መልሼ ስጠይቸው፡- «ምኑ ነው ግልጽ ያልሆነላችሁ? እንዴትስ ነው ነገሩ ያልገባችሁም? ወይስ እንዲገባችሁ አልፈለጋችሁም? በርግጥ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሰው ሁሉ ዛሬ ተነሥቶ ዘረኛ የሆነ መሰላችሁ? ይኼንን ሁሉ ሕዝብ ለዚህ ቁጣ ያበቃው ምን ይመስላችኋል? አዎ፣ ሰላምማ ይሻላል። ከሰላም የሚበልጥ ምንም ነገር የለም። አሁን ሕዝቡ ይኼ ጠፍቶት ነው? በሰላም ወጥቶ እንዳይገባ ያደረገው፣ ከመሬቱ ያፈናቀለው፣ ንግዱን የቀማው፣ በየእስር ቤቱ ልጆቹን የሚያሰቃይበት ተቀናቃኝ መጥቶበት እንጂ። እንዲህ ያለውን ችግር «በላ/balaa» ይለዋል ኦሮሞ። «በላ» መጥቶበት እንጂ ሰው ሰላም እንዴት ይጠላል?» ብዬ አመልስላቸዋለኹ። (’በላ’ ከሚለው ላይ – ፊደል ‘ላ’ ላልቶ ይነበብ)»

ስለዚህ ይህች መልእክት ለነዚህ «አድናቂ-ስታትስኮ» ወዳጆቼ ነው። በደንብ ብትፈትሹት፣ ሳታውቁትም ሆነ እያወቃችሁ አሁን ያለው እጅግ አስቸጋሪ ዘረኛ ሥርዓት ተመችቷችኋል ማለት ነው። ለጥቂቶችና የጥቂቶች የሆነው የዚህ መንግሥት የጥቅም ተጋሪ ናችሁ ወይም ከሚወድቅ ፍርፋሪ ተጠቃሚዎች ናችሁ። እንደዚያ ካልሆነ ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያለው የሕዝብ ቁጣ፣ የደም አበላ፣ ዕንባና ስቃይ «ይቀጥል፤ እናስቀጥለዋለን» ልትሉ አትችሉም። ስታትስኮው መቀየር አለበት፤ ለሁላችንም የሆነች ኢትዮጵያ ስትኖር፤ ሁሉም ሰው በእኩልነት ሲኖር፣ አንደኛ ዜጋ እና ሁለተኛ ዜጋ መሆን ሲቆም ሁሉም በደስታ ይኖራል።

ይህ ስታትስኮ ጥቂት የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን ስብሰባ በመጋበዝ፣ እነ ፓትርያርክ ማትያስን መግለጫ በማሰጠት፣ የዋህ ካህናትን አስገድዶ «ሕዝቡን በማስወገዝ፣ ወይም ታቦትና ጥላ አስይዞ ለሽምግልና በማስወጣት» ከለውጥ ሊተርፍ አይችልም። «ስታትስኮው ይቀጥል» ማለት በርግጥም ሕዝቡን ከመስደብ አይለይም። «ኦሮሞውም ከመሬትህ እየተፈናቀልክ፣ ልጆችህን በማዕከላዊ እያስገረፍክ፤ ጋምቤላውም መሬትህን እያስዘረፍክ፣ ሕንድና አረብ ሀገርህን እየወሰደው፤ አማራውም በቁም እስር እየተንገላታህ ኑር» ማለት ነው። እንዴት ሊሆን ይችላል? The satus quo should change.

+++++

አሁን እየሆነ ስላለው ነገር ምንም ስለማያውቄትና ምንም ማወቅ ስለማይፈልጉት ወዳጆቼ ከጥቂት ወራት በፊት እንዲህ ብዬ ነበር።

«አለማወቅ፣ አለመጠየቅ … አያኮራም። አካባቢን ለማወቅ አለመፈለግ፣ ነገሮችን ሁሉ፣ በዙሪያችን የሚከናወኑትን ነገሮች ለመገንዘብ ፍላጎት ማጣት አያኮራም። ጭራሽ ስለ አገር አለማወቅና አለመጨነቅ፣ አለመጠየቅና አለመረዳት እንዴት ሊያኮራ ይችላል? እንግሊዛዊው ገጣሚና የሥነ ጽሑፍ መርማሪ ቶማስ ግሬይ (Thomas Gray) የሚታወቅባት አንዲት የግጥሙ ቅንጣቢ ለእኛም ትሠራለች።

“where ignorance is bliss,
’tis folly to be wise.” ብሏል።
እኔም ወደ አማርኛ ስተረጉመው፦
“ድንቁርናና አለማወቅ ደስታና ፍስሐ በሆነበት፣
ማወቅና መገንዘብ ማለት እጅግ ታላቅ ጅልነት”
አልኩት።
(Thomas Gray “Ode on a Distant Prospect of Eton College”) (26 December 1716 – 30 July 1771)»

****************
“E pluribus unum = Out of many, one.”!!

ብዙዎች ስንሆን ግን አንድ ነን።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here