- Advertisement -
ነሃሴ 6 2008 ዓ ም
ዛሬ በብራዚል ሪዮ ዲጃኔሮ በተደረገው የሴቶች የ10000 ሜትር ውድድር አልማዝ አያና በርቀቱ አዲስ የዓለም ክብረወሰን በማስመዝገብ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሪዮ ኦሎምፖክ ወርቅ ሜዳሊያ አምጥታለች።
ርቀቱን ለመጨረስ የወሰደባት ጊዜ 29 ደቂቃ 17.45 ሰከንድ ነው።
የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና ጥሩነሽ ዲባባም ከወሊድ ረፍት ከተመለሰች በኋላ በኦሎምፖክ የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።
ውድድሩን ሁለተኛ ሆና የጨረሰችው ከኒያዊቷ ቪቪያን ቸሪዮት ናት።
አልማዝ አያና በዚሁ በሪዮ ኦሎምፒክ በ5000 ሜትር ርቀት የምትወዳደም ሲሆን ፤ ሁለተኛ ወርቅ ታመከለች የሚል ግምት አለ።