spot_img
Thursday, November 30, 2023
Homeዜናከትግራይ ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ

ከትግራይ ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ

advertisement

ነሃሴ 9 2008 ዓ ም

16 የትግራይ ተወላጅ አክቲቪስቶች “ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን ይውረድ የሽግግር መንግስት ይቋቋም” ሲሉ መግለጫ አወጡ
በአጠቃላይ ለ25 ዓመታት ሙሉ ህዝባችንን አፍኖ ሲገዛ የቆየና፣ ለ40 ዓመታት ሰላማዊ ዜጎችን እየረሸኑ አገራችንን እየዘረፉ የቆዩ ባለስልጣኖች ያሉበት ህወሓት/አህአዴግ በተለይ በዚህ ዓመት በኦሮሞና በአማራ ህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍቷል። የአገዛዙን የግድያ ወንጀሎች እናወግዛለን፤ የህዝቡን ተቃውሞ እንደግፋለን።

ስለዚህ በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ፣ የህዝባችን አንድነት እንዲጠናከርና የአገራችን ሉኣላዊነት እንዲከበር᎓-
1. ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን መወገድ አለበት
2. በኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበሮችና ብቃት ባላቸው ግለሰቦች የሽግግር መንግስት መቋቋም አለበት።
ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት የሚከተለውን ጥሪ እያቀረብን ፣ እኛም ከህዝባችን ጐን ተሰልፈን ለትግሉ መሳካት የአቅማችንን እንደምናበረክት ቃል እንገባለን።
1. ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮና ፋታ ሳይሰጥ አፋኙን አገዛዝ እንዲያስወግድ፣
2. በሰላማዊ ህዝብ ውስጥ የእርስ በርስ ደም መፋሰስ እንዳይከሰት ጥንቃቄ እንዲደረግ፣
3. ሰራዊቱና ሌሎች የመንግስት ታጣቂዎች በህዝባቸው ላይ እንዳይተኩሱ፣
4. ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ትግሉ እንዲጠናከር፣
5. የትግራይ ህዝብ በራሱ ላይ ብዙ ግፍ የሚፈፅመውንና በስሙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን የሚጨፈጭፈውን ህወሓት አውግዞ ከኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጎን እንዲሰለፍ
በተጨማሪ ነፃነት ባላቸው አገሮች ውስጥ እየኖሩ የግፍ ስርዓቱን ዕድሜ ለማራዘም የሚሞክሩት ግለ ሰቦች፣ በተለይም የህወሓት ደጋፊዎች አደብ ካልገዙ የኢትዮጵያ ህዝብ አንደሚፋራዳቸው እንዲያውቁ፣ ማሳሰብ እንፈልጋለን።

የስም ዝርዝር᎓
1. ህይወት ተሰማ
2. ሕሉፍ በርሀ
3. ስልጣን ኣለነ
4. በየነ ገብራይ
5. ተስፋዬ መሓሪ
6. ተስፋይ ኣፅብሃ
7. ታደሰ በርሀ
8. ነጋሲ በየነ
9. ናትናኤል ኣስመላሽ
10. ዶክተር ኣረጋዊ በርሀ
11. ኣብራሃ በላይ
12. ኪዳነማርያም ፀጋይ
13. ካሕሳይ በርሀ
14. ዘልኣለም ንርአ
15. ደስታ ኣየነው
16. ዶክተር ግደይ ኣሰፋ

በዚህ መግለጫ ይዘት ሊስማሙ ከሚችሉ ሰዎች ጋር በሙሉ ስላልተነጋገርን በዚህ የሚስማሙ ስሞቻቸውን ወደሚከተለው ኣድራሻ ከላኩልን መግለጫውን በድጋሚ እናወጣዋለን᎓:
ethiocivic@gmail.com

_____
ምንጭ : ማህበራዊ ሚዲያ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here