spot_img
Monday, October 2, 2023
Homeአበይት ዜናአትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የሬዮ ኦሎምፒክ ማራቶንን ካሸነፈ በኋላ ያሳየው የፖለቲካ ተቃውሞ ...

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የሬዮ ኦሎምፒክ ማራቶንን ካሸነፈ በኋላ ያሳየው የፖለቲካ ተቃውሞ ኢትዮጵያውያንን እና ዓለምን አነጋገረ

advertisement

ነሃሴ 15 2008 ዓ ም

ፈይሳ ሌሊሳ የኦሎምፒክ ማራቶን ውድድሩን ሲጨርስ ያሳየው የተቃውሞ ምልክት
ፈይሳ ሌሊሳ የኦሎምፒክ ማራቶን ውድድሩን ሲጨርስ ያሳየው የተቃውሞ ምልክት

ኢትዮጵያ ከዚህ ከሪዮ ኦሎሚፒክ በፊት ከተሳተፈችባቸው ኦሎምፒኮች ውጤት ጋር ሲነጻጸር የሪዮ ውጤት እየተባለ በሚተችበት ሁኔታ ፤ በመጨረሻው የአትሌቲክስ ውድድር መርሃ ግብር በወንዶች ማራቶች ኢትዮጵያዊው ፈይሳ ሌሊሳ አንደኛ ሆኖ የጨረሰውን የኬንያውን ኢሊድ ኪፕቾጌን በቅርብ ርቀት ተከትሎ በመግባት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አምጥቶ ነበር።

ፈይሳ ርቀቱን ሌመጨረስ የተወሰነ ሜትሮች ሲቀሩት ጀምሮ በኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን በተቃውሞ ምልክትነት እየታወቀ የመጣውን ተጨብጦ ተመሳቅሎ ወደላይ የተሰቀለ እጂ በዓለም መድረክ ላይ አሳይቷል። ምልክቱን “የፕሬስ ኮንፈረንስ” በሚያደርግበትም ሰዓት ደግሞታል።

በአዲስ አበባ ሊደረግ የነበረው ተቃውሞ በታፈነበት ዕለት የራሱን እጣ ፋንታ ጉዳይ ሳይል በዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያውያን ያሉበትን የአፈና ሁኔታ በማሳየቱ ብዙ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን ግልጽዋል። እንደጀግናም አይተውታል።

ፈይሳ ከውድድሩ ፍጻሜ በኋላ በሰጠው ቃለ ምልልስ ወደ ኢትዮጵያ ቢመለስ ህይወቱ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ገልጾ ፤ የፖለቲካ ጥገኝነት እንደሚጠይው የሚጠቁም ፍንጭ ሰቷል።

ማምሻውን ፈይሳ ሌሊሳ ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ “አስቤበት ያደረኩት ነው፤ ብሞትም አይቆጨኝም በማለት” ያደረገው ያመነበትን ነገር እንደሆነ ተናግሯል።

ለፈይሳ ሌሊሳ መርጃ የሚሆን የገንዘብ ማሰባሰብ “GO FUND ME” ድረ ገጽ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ተጀምሯል።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,723FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here