ነሃሴ 18 2008 ዓ ም

በፌደራል ፖሊስ ማንነት ተከልለው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ከጎንደር አንገርብ እስር ቤት ለመውሰድ የሞከሩ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠማቸ ተሰማ።
በዚሁ ሳቢያ የህወሓት ታጣቂዎች በአንድ በኩል ፤ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የታሰሩበት በጎንደር ከተማ የሚገኘው የአንገርብ እስርቤት ጠባቂ ፖሊሶች እና የጎንደር ህዝብ በሌላ በኩል ሆነው ጦርነት ወደሚመስል የተኩስል ልውውጥ እንደገኑም ለማወቅ ተችሏል።
የደረሰው የጉዳት መጠን እስካሁን ባይታወቅም ፤ ህወሓት በርካታ ሰራዊት ከሄሊኮብተር ጋር እንዳሰለፈ ለማወቅም ተችሏል።
በርካታ ልምድ ያላቸው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪዎች ሃገር ጥለው ከወጡ በኋላ ፤ አየር ኃይሉ ታማኝ ናቸው ተበለው በሚታሰቡ የህወሓት ምልምሎች እንደወደቀ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ከዚህ በፊት ያሳወቁት ጉዳይ ነው።
ይሄ ማለት በጎንደር ላይ የዘመተው እግረኛውም፤ አየር ኃይሉም የህወሓት እንደሆነ ይጠቁማል።
መሰረታዊ ፖለቲካዊ እና ሌሎች የመብት ጥያቄዎች እንዳሉ ሆኖ ፤ የጎንደሩን ታሪክ የማይረሳው ህዝባዊ አመጽ የቀሰቀሰው የህወሓት ሰዎች የወልቃይት የማንነት ጉዳይ ኮሚቴ አባል የነበሩትን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በህገወጥ መንገድ ሌሊት ከቤታቸው ለመውሰድ ባደረጉት ሙከራ መሆኑ ይታወሳል። ኮሎኔሉ ራሳቸውን ለመከላከል ባደረጉጥ ትግል ተኩስ በከፈቱባቸው የህወሓት ሰውች ጋር ተታኩሰው ሁለቱን ገድለዋቸዋል።
ህዝቡ የኮሎኔል ደመቀ ጉዳይ በህግ መታየት ካለበትም የሚታየው በጎንደር ፍርድ ቤት ነው ባይ ሲሆን ፤ የህወሓት ሰዎች ነገሩብ በእብሪት አይተው “ልክ እናስገባለን” የሚለውን አስተሳሰባቸውን ስራ ላይ ለማዋል እየሞከሩ ብሱ ሰላማዊ ሰው እየጨረሱ ነው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጂት በሲቪሎች ላይ የደረሰውን ግድያ ለማጣራት የህወሓትን መንግስት ቢጠይቅም ፤ ለጥያቄው አሉታዊ ምላሽ ተሰጥቶታል።
___
ቦርከና ላይክ እና ሼር ማድረግ አይርሱ።