- Advertisement -
ነሃሴ 19 2008 ዓ . ም

በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ የወራትን ዕድሜ ካስቆጠረው ህዝባዊ አመጽ ጋር የተያያዘ ጠንካራ ተቃውሞ በቡሬ ጎጃም እና በሰሜን ጎንደር የተለያዮ ከተሞች እንደተከሰቱ ከተጠቀሱት አካባቢዎች ምንጭ ያላቸው ኢትዮጵያውያን በማህበራዊ ድረ ገጽ ከዘገቡት እና ከኢሳትም ዘገባ ለማወቅ ተችሏል።
በቡሬ የተከሰተው አመጽ ከብአዴን ጋር ንክኪ ያላቸውን የንግድ ተቋማት ኢላማ በማድረግ ጥቃት እንዳደረሰም ለማወቅ ተችሏል።
እንደ ኢሳት ዘገባ በዛሬው የቡሬ አመጽ አንድ ሰው የተገደለ ሲሆን ፤ ያልታሰበውን አመጽ ለመቆጣጠር ተጨማሪ ሰራዊት ከባህር ዳር ተልኳል። በተያያዘ ዜና ትላንት በፍኖተ ሰላም ጎጃም በነበረ አመጽ አወቀ ሙሴ የሚባል የኮሌጂ ተማሪ ተገድሏል እንደኢሳት ዘገባ።
ተመሳሳይ አመጽ በሰሜን ጎንደር ትንንሽ ከተሞች እየተቀጣጠለ ለህወሓት አስተዳደር ስጋት እየደቀነ ነው።