spot_img
Thursday, May 30, 2024
Homeነፃ አስተያየትየትናንትናው የወያኔ መግለጫ የህዝባችንን ትግል የበለጠ የሚያቀጣጥል ነዳጅ ነው!

የትናንትናው የወያኔ መግለጫ የህዝባችንን ትግል የበለጠ የሚያቀጣጥል ነዳጅ ነው!

አቻምየለህ ታምሩ በፌስቡክ ገጹ እንደጻፈው
ነሃሴ 22 2008 ዓ ም

ከደቂቃዎች በፊት ወያኔ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ያወጣውን የትናንትናውን የጭንቅ መግለጫውን እያነበብሁ ነበር። ወያኔ «አምስት ቀን ሙሉ ተወያይቼ አወጣሁት» ባለው በዚህ የትናንትና መግለጫው ያስተማረን ነገር ቢኖር አምስት ቀን ሙሉ በዝግ ሲወያይ ከርሞ አንድም እንኳ የህዝቡን ጥያቄ አንስቶ አለመወያየቱን ነው። ወያኔ አሉብኝ ብሎ ያነሳቸው ችግሮች አንድም ቦታ በህዝብ የተነሱ ጉዳዮች አይደሉም። ወያኔዎች አንድ ሳምንት ሙሉ ተሰብስበው የሰነበቱት ህዝብ ባነሳቸው ጥያቄዎች ዙሪያ መፍትሄ ለመስጠት ሀሳብ ሲያወጡ ሲያወርዱ ሳይሆን እንደለመዱት ህዝቡን እንዴት መሸወድና ማዕበሉን ማለፍ እንዳለባቸው፤ የትግራይንም የበላይነት እንዴት እንዳዲስ ማጠናከር እንዳለባቸው ሲዶልቱ ነው።

በእውነቱ ወያኔዎች ያወጡት ይህ የትናንትናው መግለጫቸው ህዝባችን በነሱ ላይ የመጨረሻ ተስፋ እንዲቆርጥና መፍትሔ በራሱ መውሰድ እንዲጀምር የሚያበረታታና ለበለጠ ተጋድሎ እንዲነሳ ጉልበት የሚሆን መልካም አጋጣሚ ነው። ይህ የወያኔ መግለጫ ቀድሟቸው ለሄደው ህዝባችን ካሁን በኋላ እነሱ በጎ ስራ ሰርተው ሊጠቅሙት የማይችሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሱ እንዲያውቅ አስችሎታል።

ገገማዎቹ የትግራይ የገበሬ ወታደሮች ያንን ሁሉ ንጹህ ሰው በግፍ ገድለው ዛሬም ምንም ነገር እንዳልተፈጥረ በመቁጠር እንደለመዱት ህዝቡ ያልጠየቀውን ጥያቄ ራሳቸው እያነሱና ራሳቸው እየመለሱ ያላግጣሉ። ህዝቡ ቀድሟቸው እንደሄደ ግን ዛሬም አልተገለጠላቸውም። ቀድሞ የሄደን ህዝብ፤ ልቡ የሸፈተን እልፍ በተለመደው መንገድ መሸወድ አይቻልም። ወያኔዎች ያልገባቸው ነገር ቢኖር ይህ ነው! ዛሬም እንደ ትናንቱ በተመሳሳይ መንገድ ህዝቡን መሸወድ የሚችሉ ይመስላቸዋል። ዛሬም ያንን ሁሉ ንጹህ ሰው ገድለው ሀያ አምስት አመታት ሙሉ ስንሰማው በኖርነው የተለመደ ማታለያቸው በደረቁ ሊላጩን ይሞክራሉ! ዛሬ ላይ እንደትናንቱ አጭበርብረው የሚሰጡት መግለጫቸው የበለጠ ህዝቡ ተስፋ እንዲቆርጥ የሚያደርግ መሆኑና ትግሉን የበለጠ ወደማይቀለበስበት ደረጃ የሚያደርስ ሞተር መሆኑን አልተገነዘቡትም። ወያኔዎቹ እንዲህ አይነት መግለጫ ቶሎ ቶሎ ቢያወጡል የደስታችን ቀን ቅርብ ይሆናል!

በትናንትናው የወያኔ መግለጫ ግን የአማራ ተጋድሎ ፍሬ እንዳፈራ በግልጽ ማየት ይቻላል። በጎጃምና ጎንደር «አማራነት ይከበር!» እያሉ በግፍ የወደቁት ሰማዕቶቻችን ዛሬ ትግላቸው ፍሬ አፍርቶ በደማቸው በጻፉት ታሪክ በሀያ አምስት አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ወያኔ አማራን አስመልክቶ መግለጫ ሲያወጣ «ትምክትና የድሮ ስርዓት ናፋቂ» በሚል ለአማራ የሰጣቸውን ስያሜዎች ሳይጠቀም መግለጫ ማውጣቱን ተመለከትን። ለወትሮው ወያኔ አማራን አስመልክቶ መግለጫ ሲያወጣ «ትምክተኞች፣ የድሮ ስርዓት ናፋቂዎች፣ ነፍጠኞች…» ወዘተ እያለ አማራውን ያሸማቅቅ ነበር። የራሱን ታሪክ እየጻፈው ባለው የዚህ ዘመን የአማራ ትውልድ ተጋድሎ ግን ወያኔ እየቀፈፈውም ቢሆን ያለ ተፈጥሮው እኛን ትምክህተኛና የድሮ ስርዓት ናፋቂዎች ማለቱን ትቶታል።

ተጋዳዩ ህዝባችን አንድ ነገር ማወቅ አለበት። ዛሬ አማራው ከወያኔ እየጠየቀ ያለው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ አይደለም። ዛሬ አማራው የዲሞክራሲ ጥያቄ አላነሳም። የዛሬ የአማራ ችግር የህግ የበላይነት አለመኖር አይደለም። እነዚህ ዲሞክራሲያዊ ጉዳዮች ዛሬ ለአማራው የቅንጦት ጥያቄዎች ሆነዋል። የዛሬው የአማራ ቀዳሚ አጀንዳ ራስን ከፈጽሞ ጥፋት የማዳን የህልውና ጉዳይ ነው። አማራ የሚታገለው ስልጣን ለመያዝ ሳይሆን ራሱን ከፈጽሞ ጥፋት ለማዳን ብቻ ነው። የመልካም አስተዳደር፤ የዲሞክራሲና የህግ የበላይነት ጉዳዮች የአማራው ህልውና ሲረጋገጥ የሚያነሳቸው ጉዳዮች ናቸው። የአማራው የህልውና ችግር መንስኤ ራሱ ወያኔ ነው። ስለዚህ የአማራ ችግር የሆነው ራሱ ችግሩ [ማለትም ወያኔ] የአማራን ችግር ሊፈታ አይችልም። ስለሆነም የአማራ ችግር በወያኔ የሚመለስ አይደለም። የአማራ ችግር የሚፈታው ነቀርሳው ወያኔ ሲወገድ ብቻ ነው።

ወያኔ ተንሰራፍቶ ያለውን የትግሬ የበላይነት የበለጠ ለማስጠበቅ የአማራ ህዝብ ያልጠየቀውን እንመልሳለን ብለው አንድ ሺህ አንድ ጊዜ መግለጫ ቢያወጡ የአማራን ተጋድሎ ሊያስቆሙት አይችልም። የንጹሀን አማሮች ተጋድሎ በትግራይ ሰይጣኖች ሽንገላ ፈጽሞ ሊቆም አይችልም። እደግመዋለሁ የአማራ ተጋድሎ ወያኔ ያልበላውን ስላከከ አይቆምም። ይህንን ጠላትም ወዳጅም ማወቅ አለበት።

በመጨረሻ ግን ወያኔ ዛሬም እንዴት እንደሚያላግጥ ከትናትናው መግለጫው መካከል የሚከተለውን «የመፍትሔ ሀሳብ» ተመልከቱ…

«በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደርና በአጎራባች የትግራይ ወረዳ መካከል ከወሰን ማካለል ጋር ተያይዞ በተነሳው ጉዳይ በህወሓትና ብአዴን አመራር በኩል መፍትሄ ከመስጠት አኳያ የተከሰተው መዘግየት ተገቢ እንዳልሆነ ገምግሟል። ሁለቱ ድርጅቶች ከዚህ ድክመት ተላቀው ፈጣንና ህዝብን ማዕከል ያደረገ መፍትሄ እንዲሰጡም ነው የወሰነው። በትግራይ ክልል ከወልቃይት ጋር ተያይዞ የተነሳው ጥያቄ በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ተከትሎ እንዲታይም ወስኗል።»

ይታያችሁ መግለጫው የወልቅይትን ችግር የብዓዴንና የህወሀት አመራር መፍትሔ ሳይሰጡ ስለቀሩ የተከሰተ ነው ይልና መፍትሔውን ግን ህወሀት ብቻ እንዲሰጥ ያዝዛል! በየትኛው አለም ነው የመፍትሄው አካል ያልሆነ አካል የችግሩ መንስኤ ሊሆን የሚችለው? እንዴት ብሎ ነው የወልቃይት ችግር የብዓዴንና የህወሀት አመራር መፍትሔ ሳይሰጡ ስለቀሩ ተከስቶ መፍትሔው ግን በህወሀት ብቻ ሊሰጥ የሚችለው? ህዝቡኮ አደባባይ አንድም «የትግሬ የበላይነት ይብቃ» ብሎ ነው። ወያኔ ግን በዚህ ህዝቡ ከዳር እስከዳር ተነስቶ «የትግሬ የበላይነት ይብቃ» እያለ ባለበት ያሁኑ ወቅት እንኳ የትግሬ የበላይትን በአዋጅ ይደነግጋል! በእውነቱ ከዚህ በላይ የአፓርታይድ ስርዓት ምን አለ?

ከፍ ብዬ በጠቀስኩት የወያኔው መግለጫ መሰረት የወልቃይትን ጉዳይ ይፍታው የተባለው የትግራይ ክልል በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምትና በሁመራ አማራን ሲገድል የኖረውን ግፈኛ ቡንድ ነው! በወያኔው መግለጫ መሰረት የወልቃይትን ጉዳይ ይፍታው የተባለው የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላትን ከጎንደር አፍኖ የወሰደውን አረመኔዊ ቡድን ነው! በወያኔው መግለጫ መሰረት የወልቃይትን ጉዳይ ይፍታው የተባለው የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮምቴ አባላት ትግራይ ሄደው «አይናችሁን እንዳላይ!» ብሎ ያባረረውን አስተዳደር ነው። በወያኔው መግለጫ መሰረት የወልቃይትን ጉዳይ ይፍታው የተባለው የትግራይ ክልል በህገ አራዊቱ መሰረት ጥያቄ ቀርቦለት አልፈታም ካለ ፌድሬሽን ምክር ቤት መፍታት ይኖርበታል የተባለውን ጉዳይ ነው። በወያኔው መግለጫ መሰረት የወልቃይትን ጉዳይ ይፍታው የተባለው የተባለው የትግራይ ክልል የወልቃይት ጉዳይ ቀርቦለት መፍታት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ጉዳዩ ወደ ፌድሬሽን ምክር ቤት ካመራ በኋላ ወደኋላ አይመለስም የሚለውን ህገ አራዊታዊ አንቀጽ ተጥሶ ነው። ለወያኔ ሲሆን ሁሉም እንስሳት እኩል ናቸው- አንዳንዶች ደግሞ የበለጠ እኩል ናቸው። ህዝቡ ሰልፍ የወጣው «የትግራይ የበላይነት በቃን» ብሎ ነበር! ወያኔ ግን ሰልፍ ለወጣው ህዝብ ባወጣው መግለጫ የሰጠው የመፍትሔ ሐሳብ የትግራይ የበላይነትን ህጋዊ ማድረግ ነው!

ባጭሩ የወያኔው የትናንትና መግለጫ ህዝቡ ካነሳው «የትግራይ የበላይነት ይብቃ» ከሚለው አገራዊ ጥያቄ ጋር ፊት ለፊት የሚላተም ነው። ህዝባችን በነቂስ ወጥቶ «የትግሬ የበላይነት ይብቃ» ሲል ወያኔ ግን ለዚህ ጥያቄ የሰጠው መልስ የትግራይን የበላይነት በጽኑ መሰረት ላይ ማስቀመጥ ነው። በቤተ ወያኔ «የትግሬ የበላይነት በቅቶናል!» ለሚለው ህዝባዊ ጥያቄ የሚሰጠው ግብረ መልስ የትግሬን የበላይነት ሽቅብ ገንብቶ አማራውን ግን የበለጠ ቁልቁል መግፋት ነው። ይህ የመለስ ርዕይ 101 ነው።

____
ጸሃፊውን በፌስቡክ ላይ ማግኘት ይቻላል

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here