ነሃሴ 25 2008 ዓ ም

የፖለቲካ ድጋፍ መሰረቱ ትግራይ ላይ የሆነው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መንግስት ወታደራዊ ዘመቻ ለማድረግ በ”ፌደራል” መንግስት በኩል የማደናገሪያ ውሳኔ ካስሰነ በኋል በታላቁ የአማራ ነገድ ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ አፋፍሞ ቀጥሏል።
ከትላንትና ወዲያ የአማሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛ አገልግሎት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጂት (መኢአድ) እና የአይን ምስክሮችን ጠቅሶ በዚህ ሳምንት ከሰኞ በፊት በነበሩ ሁለት ቀናቶች ብቻ አማራ ተብሎ በተከለለው ክልል ቢያንስ 45 አምስት ሰዎች ተገድለዋል። ነገር ግን በሳምንቱ ማለቂያ ላይ በአማራ ክልል በርካታ ከተሞች የነበረውን ውጥረት እና የተሰማራውን የጦር ኃይል ግምት ውስጥ ሲገባ ፤ የጉዳቱ መጠን በዛ ብቻ የተወሰነ ነው ለማለት እንደማይቻል የሚናገሩ የፖለቲካ እና ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች አሉ።
የአማራ ነገድ ተሟጋቾች በክልሉ በየከተሞች ከህዝብ ወገን ከሆኑ ነዋሪዎች ባላቸው ፈጣን ግንኙነት ምክንያት በደረሰው ጉዳት ጋር በተያያዘ የሚያቀርቡት መረጃ የተሻለ እንደሆነ ይሄ ድረ ገጽ ያምናል።
ሙሉቀን ተስፋው በማህበራዊ ሚዲያ ባቀረበው መረጃ መሰረት ትላንት በባህር ዳር የሰባታሚት እስር ቤት ያላግባብ የታሰሩ ሰዎችን ለማስፈታት ገበሬዎች ባደረጉት ትግል ጋር ተያይዞ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች በጂምላ ያለርህራሄ ተጨርሰዋል።
ዛሬ ደሞ የህዝባዊ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መንግስት ሰራዊት በሰሜን ጎንደር መተማ ከፍተኛ እልቂት አድርሷል። እስካሁን በማህበራዊ ሚዲያ በወጣው በምስል የተደገፈ መረጃ መሰረት በመተማ ከተማ ብቻ ከአስር በላይ ሰላማዊ ዜጎች ተገድለው በሃያወች የሚገመት ቁጥር ያላቸው እንደቆሰሉ ለማወቅ ተችሏል። የህወሓት መንግስት የድንበር ጸጥታ ለማስከበር በሚል ሺፋን በሱዳኑ አልባሺር መንግስት ጋር የጋራ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ስምምነት ማድረጋቸው ይታወሳል። ዛሬ ከመተማ አካባቢ የትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የተነሳውን ህስባዊ አመጽ ተከትሎ ወደ ሱዳን እንደገቡ የሚናገሩ ወገኖችም አሉ ፤ ሁኔታውን ለሌላ ወገን ለማጣራት ባይቻልም። የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በየዓመቱ በዓሉን ትግራይ ላይ ሲያከብር ርዕሰብሄሩን አልባሺርን ጨምሮ የሱዳን ባለስልጣናት ግንባር ቀደም ታዳሚዎች እንደሆኑ ሚስጥር አይደለም።
ባለፈው ሳምንት መገባደጃ አካባቢ ህወሓት ለሽፋን የሚጠቀምበትን የኢሃዴግ ፓርቲ ለግምገማ አስቀምጦ ባለፈው 15 ዓመት ብዙ ስራ ሰርቻለሁ ፤ በህብረተሰቡ እና አጋር በሚላቸው ድርጂቶች ግን የመንግስት ስልጣን ምንነት ግንዛቤ የለም የሚል አቋም አንጸባርቋል። ነገሩ ያስቆጣቸው ኢትዮጵያውያን ደሞ የመንግስት ምንነት ጽንሰ ሃሳብ ያልገባው የመንግስት ስልጣንን የሃብት ማካበቻ እና የጎሳ የበላይነት መገንቢያ ያደረገው መሰረቱን በትግራይ ህዝብ ላይ ያነጸው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ እንጂ ፤ የሶስት ሺህ ዘመን የመንግስትነት ታሪካ ውጤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም ባይ ናቸው ።
ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢሃዴግን ጉባኤ መጠናቀቅ ተከትሎ ፤ የህወሓት ፍላጎት ለማሳካት በሚመስል መልኩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በአማራ ነገድ ላይ እንዲዘምት አዘዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመቶዎች የሚገመቱ የሰራዊቱ አባላት በህዝብ ላይ እየተፋፋመ ያለውን የጂምላ ግድያ በመቃወም እየከዱ ከህዝቡ ጉን እየተሰለፉ እንደሆነም ተሰምቷል።
በመንግስት ላይ በቁርጠኝነት የተነሳው የአማራ ነገድ ብቻ አይደለም። በመላው ኢትዮጵያ ጸረ መንግስት ዓመጽ ተቀጣጥሏል። የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ አማርኛ አገልግሎት ክፍል እንደዘገበው በኮንሶ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተዘግተዋል። በብዙ የአማራ ክልል ከተሞችም የመንግስትን መዋቅር በማፈራረስ ህዝቡ ራሱ በመረጣቸው የጎበዝ አለቆች እየተመራ እንደሆነ ታውቋል።
እስካሁን ከትግራይ በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ በህዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ በርካታ ዜጎች ተገድለዋል።
ቦርከና