spot_img
Monday, May 29, 2023
Homeአበይት ዜናቅሊንጦ እስር ቤት ተቃጠለ ፤ ሃያ ያህል ሰዎች ከተኩስ ሩምታ ጋር በተያያዘ...

ቅሊንጦ እስር ቤት ተቃጠለ ፤ ሃያ ያህል ሰዎች ከተኩስ ሩምታ ጋር በተያያዘ ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ተሰምቷል

- Advertisement -

ነሃሴ 28 ፤ 2008 ዓ ም

ዛሬ ጧት ላይ ቅሊንጦ እስር ቤት በእሳት እንደተቃጠ በሰዓቱ በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞችን ጠቅሶ ኢሳት ዘግቧል። ለኢሳት መረጃውን ያደረሱት ወገኖች በአካባቢው ከፍተኛ የተኩስ ሩምታ እንደነበረም ጨምረው ገልጸዋል። ከኢሳት ቪዲዮ እንደሚታየው መረጃ የሰጡት ሰዎች ከእስር ቤቱ በቅርብ ርቀት ነበሩ፤ ሆኖም በነበረው የተኩስ ሩምታ እና በአካባቢው በነበረ የፖሊስ ኃይል ምክንያት ወደ እስር ቤቱ ግቢ መጠጋት አልተቻለም።

አዲስ ፎርቹን እንደዘገበው ደሞ ከነበረው የተኩስ ልውውጥ ጋር በተያያዘ ሃያ ያህል ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀሩ ታውቋል። የእሳት አደጋ መከላከያ ከአዲስ አበባ የመጣ ሲሆን ፤ ሶስት ያህል እሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፖታል ገብተዋል ሲል የአዲስ ፎርቹን ዘገባ አክሎ ገልጿል።

ቅሊንጦ እስር ቤት እንደ በቀለ ገርባ ያሉ በጣም ታዋቂ የፖለቲካ እስረኞች ያሉበት እና በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠበቅ እስር ቤት ነው። የኦሮሞ የፖለቲካ መሪዎች መንግስት በሶስት ቀን ውስጥ በቀለ ገርባ ስላለበት ሁኔታ ካላሳወቀ እና ለህዝብ ካላሳየ ከፍተኛ የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,864FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here