ድሜጥሮስ ብርቁ
ነሃሴ 29 2008
የወያኔ መንግስት ውሸት ከሚገኙባቸው ብዙ መንገዶች አንዱ ወያኔ የሚጨፍርበት የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን (አሁን ኢቢሲ) አንድ አማራጭ ነው። ሰሞኑን የኢቢሲን ዘገባ በፌስ ቡክ ስከታታል የኮንቴንት አቀራረቡ ለየት ያለ መስሎ ተሰማኝ።
ትንሽ የስነ ልቦና ጠበብትም ፈላልገው ምን አይነት አቀራረብ እና ኮንቴንት ተሻለ የአንባቢ ቁጥር ሊያመጣ ይችላል በሚለው ላይ ሳይሰሩ የቀሩ አይመስልም። ለምሳሌ “ስላልተረጋገጠ ወሬ” ውይይት የሚጋብዝ ፖስት ፖስተው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቀውስ ( ወያኔ ስንት ህዝብ የፈጀነት) በተወሰነ ደረጃ “ያልተረጋገጠ ወሬ” ከመስማት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ሊያሳዮ ሞክረዋል! ለየት ያለም የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ መሆኑም ነው።
ዛሬ ደሞ እዛው ገጽ ላይ ሌላ ቪዲዮ ሳይ አንድ ህጻን ልጂ ለደለበ በሬ በእጁ የበቆሎ ቅጠል ነገር እያጎረሰ ፤ የደለበው በሬ የመጨረሻውን አፉ ላይ ካደረገ በኋሏ ህጻኑን ወግቶ መሬት ላይ ሲያስቀምጠው ያሳያል። ለቪዲዮው የተሰጠው ርዕስ “ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ” !
ባንድ በኩል ወቅት ሳይመርጥ መገልፈጥ የሚወድ ሰው ስላለ ያንን ኦዲየንስ በማበራከት እንደተለመደው ወጣቶች ኢትዮጵያን ሊያጠፋ ከተቃረበው የወያኔ ፖለቲካ ይልቅ ወደ ወደ ግዴለሽነቱ ለመውሰድ ያህል ነው። በሌላ በኩል ደሞ ልክ እንደዛ እንደበሬ እያጎረሱ የያዙት ካድሬ እና ኮካ በስነልቦና ወጋ ለማድረግም ይመስላል።
የወያኔ አዲስ የፕሮፖጋንዳ አቀራረብ የመልስ ምት ይፈልጋል፤ መሬት ላይ ያለው ትግል እንዳለ ሆኖ ፤ የማንቃት እና የማደራጀት ስራ እንዳለ ሆኖ የተቀናጀ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አመላካች ይመስለኛል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ወያኔ ያሰማራቸውን እንደ ዳንኤል ብርሃነ ያሉትንም ሰዎች ወያኔ ለሚያጎርሳቸው የፖለቲካ “ከብቶች” መተው ያስፈልጋል። ሌላ ሰው አንስቶታል ይሄን ሃሳብ ትክክለኛ ይመስለኛል።
***
በሌላ ርዕስ የታምራት ላይኔን አዲስ ቃለ ምልልስ አዳመጥኩት። እንደብዙ ኢትዮጵያውያን ገና ሰውየውን ሳየው ደስ የማይል ስሜት ነው የተሰማኝ። እንደምንም ከፍቸ ያለውን ሳዳምጠው ፤ ምንም እንኳን እሱ ራሱ የወያኔ ፊትአውራሪ ሆኖ በአማራ ህዝብ ላይ ቅጥ ያጣ ጥላቻ ቢሰብክም ፤ በዚህኛው ኢንተርቪው ያነሳቸው ጥቂት ቁምነገሮች አሉ። ከማንም በላይ የወያኔ “የፖለቲካ ከብቶች” ፖከ፤ኮካ (whatever) ዲያዳምጧቸው የሚጠቀሙ ይመስለኛል። ለወያኔ ስልጣኑን ባያድኑለትም ፤ ቢያንስ ሃገር ምድር ሳይጨርስ ራሱን የሚያድንበትን መንገድ የሚጠቁሙ ይመስለኛል። “የኢትዮጵያ ህዝብ ቂመኛ አይደለም” ብሏቸዋል፤ ትክክል ነው። ይሄን ለመናገር ከሱ የተሻለ ሰው ያለ አይመስለኝም።
ቦርከና
ቦርከናን ላይክ ያድርጉ ፤ ሼር ያድርጉ