ነሃሴ 29 ፤ 2008 ዓ ም
ደሴ ገና ህወሓት ሲገባ ጀምሮ ደም ያፈሰሰባት ፤ ለረዝም ዘመን በተቀለደበት የምርጫ ጨዋታ እንኳን ከመጨረሻዎቹ ሁለት ምርጫዎች በስተቀር ገዥው ፖርቲ ብዙ ጊዜ የተሸነፈባት ከተማ ብትሆንም በቅርቡ በአማራ ክልል ከተቀጠለው ጸረ ወያኔ ትግል በዝምታ ተውጣ ብዙዎችን አስገርማ ነበር።
ምክንያቱን ለማጣራት የተደረጉ ሙከራዎች በሁለት አቅጣጫ ፍንጭ ሰጥተዋል። አንደኛው ደሴ ውስጥ ከነባሩ ይልቅ ከሌላ ቦታ የመጣ ሰው ስለሚበዛባት መፈራራት አለ የሚል ሲሆን ፤ ሌላኛው ማህበራዊ ተጽዕኖ የነበራቸው ወጣቶች ወይ ከተማዋል ለቀው ወደ ሌላ አካባቢ በመሄዳቸው እና የተቀሩትም በስራ እጦት ምክንያት የወያኔ ጎራ ስለተቀላቀሉ ነው የሚሉ መላምቶች ተሰጥተዋል።
እንደዚያም ሆኖ ትላንት ደሴ በቤት ውስጥ የመዋል አድማ ለማድረግ ሞክራለች፤ ተከፍተው የነበሩ የንግድ ቤቶች ቢኖሩም ሙሉ በሙሉ ከዥው ፖርቲ ጋር ቁርኝት የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ቁርኝት ያላቸው ወገኖች እንደነበሩ ከስፍራው የወጡ ምንጮች ያስረዳሉ።
የፌደራል ፖሊስ ( በፎቶ ላይ እንደሚታየው) በመንደር ውስጥ ወከባ እንደፈጠረም ታውቋል። በቀጣይነት ደሴ በአመጽ በመቀጠል ገዠው የህወሓት መንግስት በአማራ ክልል በንጹሃን ዜጎች ላይ ያደረገውን የጂምላ ግድያ እንደሚቃወም “አማራ ሪዚዝታንስ” በመባል ከሚታወቀው የፖለቲካ አመራር ቡድን ገጾች ለማወቅ ተችሏል።