spot_img
Wednesday, June 7, 2023
Homeአበይት ዜናዘማሪት እማዋይ ብርሃኑ የህወሓት የግፍ ግድያ ሰለባ

ዘማሪት እማዋይ ብርሃኑ የህወሓት የግፍ ግድያ ሰለባ

- Advertisement -

ጳጉሜ 5 2008 ዓ ም

እማዋይሽ ብርሃኑ ፤ ህወሃት በጎንደር በግፍ  ከገደላቸው አንዷ
እማዋይሽ ብርሃኑ ፤ ህወሃት በጎንደር በግፍ ከገደላቸው አንዷ

ህወሓት በአማራ ላይ ያለው ጥላቻ እስከምን ድረስ እንደሆነ ከተገለጠባቸው ሁኔታች አንዱ የሐምሌ ወር መጀመሪያ ጅምሮ በአማራ ክልል ሰላማዊ ተቃውሞ ላይ የወያኔ ሰራዊት ሰራዊት የወሰደው የግፍ ርምጃ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ።

ጎንደር ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ሰልፍ ከምንም ነገር በላይ ሰላማዊ እንደነበር ዓለም ዓቀፍ የዜና ተቋማት ሳይቀሩ በስፋት የዘገቡበት ጉዳይ ነው። ህዝቡ ያለውን ጥያቄ (የለውጥ ጥያቄን ጨምሮ ) በተጀመረው ሰላማዊ ሁኔታ እንዳይቀጥል የተኩስ ሩምታ በመክፈት ህወሓት ወደ ደም ጎርፍ ቀይሮታል። ህጻናት ፤ አረጋውያን እና ሴቶች ሳይቀር የግድያው ሰለባ ሆነዋል። በገፍ ወዳልታወቀ ቦታ የወሰደው ሰው ቁጥር አይታወቅም። የጉዳቱ መጠን በተለይም የሞተው ሰው ቁጥር በሙሉ ታውቋል ማለት ባይቻልም፤ ከአማራ ተጋድሎ እንቅስቃሴ በማህበራዊ ድረ ገጽ ካካፈሉት መረጃ በአማራ ክልል ከተገደሉት ከ70 በላይ ስም እንደታወቀም የሚታወስ ነው።

እማዋይሽ ብርሃኑ በጎንደር ህወሓት ካደረሰው የግፍ ግድያ ሰለባዎች አንዷ ናት። የ ሃያ ሶስት ዓመቷ ወጣት እማዋይሽ በጎንደር ከተማ የቅዱስ ዩሐንስወልደ ነጎድጓድ ዘማሪ እና አገልጋይ እንደነበረች መረጃውን ካቀበለችው ከሊያ ፋንታ ለመረዳት ተችሏል።

የእማዋይሽ ቤተሰብ ከእማዋይሽ እህት ሞት ጋር በተያያዘ ሃዘን ላይ የቆየ ሲሆን እና ወያኔ በእማዋይሽ ላይ ባደረሰው የግፍ ግድያ ምክንያት ተጨማሪ የሃዘን ድባባ በቤተሰቡ ላይ ነግሷል።

እማዋይሽ በ ጎንደር የተቃውሞ ወቅት ችግረኛ ለሆኑ የከተማው ነዋሪዎች ምግብ ሰተሻል ተብላ ነው የተገደለችው። መረጃውን ካቀበለችው ሊያ ፋንታ ለመረዳት እንደተቻለው ዜናው እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የህወሓት አጋዚ ሰራዊት የእማዋይሽን አስከሬን ለቤተሰቦቿ እንዳይሰጥ በመከልከሉ እንደእምነቱ ስርዓት ጸሎተ ፍትሃት ተደርጎላት ቤተሰቧ የቀብር ስነ ስርዓቷን ሊያከናውን አልቻለም።

እማዋይ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ነዋሪ ነበረች።

ቦርከና
__

ቦርከናን ላይክ ያድርጉ ፤ ዜናዎችን ሼር ያድርጉ።
መረጃ ለመስጠት በeditor@borkena.com ይላኩ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,879FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here