advertisement
መስከረም 2 2009 ዓ ም
በጎጃም እና ጎንደር አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት የሚገኙ መነኮሳትእና ካህናት በአቡነ ማትያስ የሚመራውን ሲኖዶስ ከእንግዲህ በኋላ እንደማይቀበሉት ማሳወቃቸውን ኢሳት ዘገበ።
በዚህም ምክንያት አቡነ ማትያስ በሚመሩት ሲኖዶስ እንደማይተዳደሩም ገልጸዋል።
መግለጭያውን ያወጡበት ምክንያት አቡነ ማትያስ የሚመሩት ሲኖዶስ በጎንደር እና በጎጃም በገዠው የህወሓት መንግስት ወታደሮች በግፍ ሲጨፈጨፍ ሲኖዶሱም ሆነ አባ ማትያስ እንደቀደሙት እንደ አቡነ ጴጥሮስ ያሉ አባቶች ለሃገር እና ለህዝብ ወገን ሆኖ ድምጽ እና ተቃውሞ በማሰማት ፋንታ ከገዳዮ ከህወሓት መንግስት ጎን በመቆማቸው እንደሆነ የኢሳት ዘገባ ይጠቁማል።
ሲኖዶሱ የሚሰጠው ምላሽ ካለ ወደ ፊት የምንዘግብ ይሆናል
____