spot_img
Sunday, June 4, 2023
Homeአበይት ዜና20 የዐማራ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ከሕዝብ ጋር ተቀላቀሉ

20 የዐማራ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ከሕዝብ ጋር ተቀላቀሉ

- Advertisement -

መስከረም 2 2009 ዓ ም

ከአዲስ አበባ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ቦሌ አየር መንገድ ሕገ ወጥ የእጽ ዝውውር ላይ አንድ ሻለቃ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ሃያ የዐማራ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው አገዛዙን ክደው ባለፈው ሳምንት ከሕዝብ ጋር መቀላቀላቸው ታውቋል፡፡ የፌደራል ፖሊስ አባላቱን ለዚህ ውሳኔ ያበቃቸው በሕዝባቸው ላይ እየደረሰ ያለው መቆሚያ ያጣ ፍጅት ነው ተብሏል፡፡

በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሠራዊት የዐማራ ተወላጆች ተለይተው መሣሪያ እንዳይዙ እንዲደረግ ሀሳብ የቀረበ ቢሆንም ስምምነት ባለመኖሩ እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም፡፡ ሆኖም የዐማራ ተወላጆችን መሣሪያ ከሰጡ በኋላ ልዩ ክትትል እንደሚደረግባቸው የዐማራ ተወላጅ የሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት ገልጸዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ደግሞ የአዋሽ አካባቢ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ሌሎች ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው አገዛዙን ከድተው መሄዳቸው ታውቋል፡፡
ዝርዝር ጉዳዮችን በቅርብ የምናሳውቅ ይሆናል!!
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!

ምንጭ : ሙሉቀን ተስፋው

_____
ቦርከናን ላይክ ያድርጉ ፤ ዜናዎችን ሼር ያድርጉ።
መረጃ ለመስጠት በeditor@borkena.com ይላኩ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,878FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here