spot_img
Wednesday, November 29, 2023
Homeነፃ አስተያየትዉህደትና ቅልቅል ለየቅል - የኢትዮጵያ ህዝብ የተዋሃደ ነው

ዉህደትና ቅልቅል ለየቅል – የኢትዮጵያ ህዝብ የተዋሃደ ነው

advertisement

ደጄኔ ላቀው
መስከረም 6 2008 ዓ ም

አንድ መሆን መለያየት አይደለም መለያየት ደግሞ አንድ መሆን አይደለም፤ ወያኔ መለያየትን እንደ አንድነት አንድነትን ደግሞ እንደመለያየት አድርጎ ይሰብካል ፤ ይህ አስተሳሰብ በዉነቱ የት ቦታ ላይ እዉነት እንደሚሆን ለማወቅ ጥረት ማድረግ አያስፈልግም ፤ በዚህ በሚታየው አለም ዉስጥ የለምና ፤ ይህ የምናየው አለም የሚተዳደረዉና የሚኖረው የእዉነትን ህግ በመከተል ነው፤ ዉሸት የምንም አይነት ነገር መተዳደሪያ ህግ አይደለም፤ በዉሸት የሚገዛና የሚኖር ተፈጥሮአዊ ነገርም የለም ። የትግራይ ወያኔ ላለፉት ፪፭ አመታት ለማድረግ የሞከረው የኢትዮጵያን ህዝብ በዉሸት ልብ ወለድ ፈጠራና የጦር መሳሪያን በመጠቀም ተፈጥሮአዊ ዉህደቱን አፍርሶ በቅልቅል መልክ ለማስቀመጥ ነበር፤ የተቀላቀለ ነገር ሁሉ ዉስጣዊ ግንኙነትና አንድነት ስለሌለው በቀላሉ መለያየትና ማፍረስ ይቻላልና። እዉነታው ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ኩሩና የረጅም ዘመናት ታሪክ ባለቤት የሆነና የተዋሃደ አንድ ህዝብ ነው፤ ለዚህም ነው የወያኔ የአስተሳሰብ እዉራን ሰወች እንዴት የተለያዩ ጎሳወች አንድ መሆን የሚችሉበት ጉዳይ ኖረ ብለው የሚያሳፍርና ሃላፊነት የጎደለው የመሪነት ሳይሆነ የአጥፊነት መንፈስ የሚያስተጋቡት ፤ ቆም ብለው ቢያስቡትና የምንለዉንም የሚሰማ ኢትዮኦያዊ አለ ብለው ያፍሩም ይፈሩም ነበር ግን ያደፈጠ ሰይጣን እንደሚባለው በተንኮላቸው ቀጥለዉበታል። ከዚህ አባባላቸው የምንማረው ወያኔወች

፩. ምንም አይነት ሃገራዊ አላማም ስሜትም እንደሌላቸውና ኢትዮጵያን ለመበታተን ሲያልሙ የሚኖሩ ተኩላወች እንደሆኑ
፪. የኢትዮጵያን ህዝብ ዉህደታዊ ማንነቱን አለማወቃቸው ነው ፤የኢትዮጵያ ህዝብ በክፉም ሆነ በደጉ፤ በመከራም ሆነ በደስታ አብሮ የኖረውና ታሪኩን በደም የጻፈው ለአስርተ አመታት ወይም ሃምሳ አመታት ተቀላቅሎ በመኖር ሳይሆን ለብዙ ሽወች በሚቆጠሩ አመታት ጊዜ ዉስጥ ዉህደትን በመፍጠር ነው፤ ይህ ታሪካዊ ዉህደቱ ደግሞ ባዶ አእምሮ ባለው የትግራይ ወያኔ ድርጅት ስሜታዊ ምኞት ሊፈርስ ወይም የፈረሰ ሊመስል አይችልም ፤ አንድ ምንም አይነት የኬሚስትሪ መሰረታዊ እውቀት የሌለው ሰው ጨዉን እንዲሁ በስሜት ብቻ ወደ ሶዲየምና ክሎሪን መበታተን አይችልምና። ጨው ለብዙ የሰዉን ልጅ ህይወት ለሚፈዉሱ ነገሮችና ምግብን ለማጣፈጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ተፈጥሮ ሁለት የተለያዩ ነገሮችን አዋህዳ ያስቀመጠችልን እጹብና ድንቅ ነገር ነው፤ የኢትዮጵያ ህዝብም እንደዚሁ በማህበራዊ ፖለቲካዊና ባህላዊ ነገሮች ታሪካዊ ዉህደትን ፈጥሮ ያለ አንድ የሆነ ጠንካራና ጨዋ ህዝብ ነው።

ስለዚህ እነዚህ የስተሳሰብ ድሃ የሆኑ የወያኔ ሰወች የኢትዮጵያን ህዝብ ለያይተን በቅልቅል መልኩ ያስቀመጥነው መስሎን ነበር ነገር ግን አሁን የሚታየው ያ ሳይሆን የበለጠ ዉህደቱን ነው፤ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ብለዉም በግልጽ በአደባባይ ተናግረዋል። በዚህም ያለማወቅ ፍርሃት የተነሳ የተኩላ ጩኸትን በሰፊው እያስተጋቡ ይገኛሉ፤ ኢትዮጵያ ወደ ሩዋንዳ አይነት እልቂት ልታመራ ትችላለች እያሉ። እንዴት ሆኖ ነው የጣሊያኑ የሙሶሎኒ የዘራፊና የከፋፋይ ሰራዊት ከኢትዮጵያ በመዉጣቱ ኢትዮጵያ የምትፈራርሰው? እንዴት ብሎ ነው የትግራዩ ሃይለስላሴ ጉግሳ ከሙሶሎኒ የተሰጠዉን የባንዳነት ስልጣኑን ስለሚያጣ ኢትዮጵያ ወደ እርስ በርስ ብጥብጥ የምትሄደው? የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ሆኖ የሚዋጋው ያንን ግፈኛ ወራሪና ባእዳን የሆነ ሰራዊት ከሃገራችን ለማጥፋት አይደለም እንዴ? እንዴት ሁኖ ነው አንድ የሆነና የተዋሃደ ህዝብ የትግራይ ወያኔ ቅጥ ያጣ የዘረፋ የአድሎና የሌብነት ድርጅት ከኢትዮጵያ ምድር ማጥፍታ ኢትዮጵያን የሚበታትነውና ወደ ሩዋንዳ ማህበራዊ እልቂት የሚወስዳት? ይህ ሰሚ ያጣን የቀበሮ የማያስፈራሪያ ጩኸታቸውን የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት በሆነው ቴሌቪዥን ብቅ ብለው የሚንተባተቡት አሳዛኝና አሳፋሪ የሆነው ኢትዮጵያን የማፍረስ አላማቸው ስላልተሳካና እንዲያዉም ወያኔ ላለፉት ፪፭ አመታት ሃገርንና ህዝብን በማፍረስ ተንኮል ስራ ላይ ተሰማርቶ ያለ ድርጅት መሆኑን ህዝብ በንድነት እየገለጸና ድርጅቱን ከሃገራችን ለማጥፋት ከምንጊዜዉም በላይ አንድ ሆነን እየተፋለምነው መሆኑን ስላወቁ ነው።

እጅግ የሚገርመው ደግሞ የሩዋንዳን አይነት ሁኔት እንዲመጣ በተንኮል ነገሮችን ሆ ብለው የፈጠሩት እራሳቸው የትግራይ ወያኔወች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚያውቅ አለማወቃቸው ነው፤ አንድን ህዝብ በጉልበት በጎሳ ክልል እንዲኖር አስገድዶ ዜጎችንም የጎሳ ማንነታቸዉን በመታወቂያ ደብተራቸው ላይ እንዲገልጹ ከማስደረግ የበለጠ የቀበሮ እረኝነት አለ ወይ? የሩዋንዳ ችግር ዜጎች በጎሳቸው ተለያይተው ማሰብና በዚያም በተነሳው ስሜታዊ ሁኔታ የተፈጸመ አሳዛኝ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እልቂት ነው፤ በዚህም መሰረት አሁን ስልጣን ላይ ያለው የሩዋንዳ መንግስት የወሰደው የመጀመሪያው እርምጃ በጎሳ አንድን ግለሰብ ወይም ህብረተስብ ለይቶ መግለጽ ወጀል እንደሆነና ይህን የሚያደርግ ግለሰብም ሆነ ድርጅት ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድበት ማድረጉ ነው፤ በተቃራኒው ግን የትግራይ ወያኔ እየጣረ ያለው ይህንን ችግር ሆን ብሎ በመፍጠርና በመሳሪያ ሃይል በማጠናከርና የችግሩን አስከፊነት ብቻ በማዉራት የማስፈራሪያ መሳሪያ ሆኖ እንዲኖር ነው – ይገርማል ። አሳዛኙ ነገር እንዴት ኢትዮጵያ በዚህ አይን፤ ማሰብንና አርቆ ማየትን የሚያስችል አእምሮ በተሳነው እጅግ የጠበበ ድርጅት ዉስጥ መግባቷ ነው ።

አስደሳቹ ነገር ግን የሩዋንዳው እልቂት ናፋቂና አፍቃሪው የትግራዩ ወያኔ ከኢትዮጵያ ምድር የሚጠፋበት ሰአት መምጣቱ ነው፤ ኢትዮጵያም ከምንጊዜዉም በበለጠ ሁኔታ አንድ ሆና ህዝቦቿን አቅፋ በክብር በሰላምና በደስታ ለዘላለም ትኖራለች።
ትግሉ ይቀጥላል!

ጸሃፊው ደጄኔ ላቀውን በፌስ ቡክ ማግኘት ይቻላል። ይሄንን ይጫኑ

____
ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ ፤ ያነበቡትን ያጋሩ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here