ቢኒ ዳና እና ታሪኩ ያስተላለፉት መልዕክት

መስከረም 7 2009 ዓ ም

ባለፉት ዓመታት በተለይ ሃገር ቤት ያሉ ተዋንያንን እና አርቲስቶች ላይ በስልጣን ላይ ያለው ለፖለቲካ ስራ ሲጠቀምባቸው ቆይቷል።

ሆኖም ኅሊና የሚባል ዳኛ አለና ባለፉት ሁለት ወራት ወደ ሺዎች የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ላይ በተለይ በኦሮሚያ ፤ እና በአማራ የተደረጉትን ዘግናኝ የወያኔ መንግስት ግድያዎች ተከትሎ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች የአዲስ አመት ዝግጂቶቻቸውን እንዲሰርዙ በጠየቁት መሰረት ብዙዎቹ አዋንታዊ ምላሽ በመስጠት ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን ያላቸውን ጥልቅ አክብሮት እና ፍቅር ገልጸዋል፤ በአንጻሩ ደሞ ( የሚረዳው ከተገኘ ) ለገዳዩ ቡድን እና ለደጋፊዎቹም የዛኑ ያህም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ያንን ፈለግ በመከተል ቀልድ በቀላቀለ የሙዚቃ ስራቸው የሚታወቁት ቢዲ ዳና እና ጓደኛው ተመሳሳይ መልስ በመስጠት መልዕክት አስተላልፈዋል። ፋይዳ ያለው ነገር ነው!

የበለጠ ፋይዳ የሚኖረው ግን ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች የህዝብ ወገን እንደመሆናቸው በስራዎቻቸው በቀጣይነት የበሰለ እና ለሃገር የሚጠቅም ስራ መስራት ሲችሉ ነው። ከግጥም ጸሃፊዎች ጀምሮ እስከ ዜማ ደራሲዎች ድረስ በቅንጂት በመስራት ሃገሩን እየተቀማ እና የዘላለም ባርነት እየተደገሰለት ያለውን ወጣት ለፍትህ እና የሃገሩ ባለቤት እንዲሆን ጊዜ ወስደው በሰል ያለ ስራ በመስራት ለመራራ ትግል የሚያነሳሳ ፤ እና የትግል ስብዕና የሚገነባ ስራ ማቅረብ አለባቸው የሚሉ ወገኖች አሉ! ለመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ የርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?

Leave a Reply

Your email address will not be published.