መስከረም 9 2009 ዓ.ም
ከዋሽንግተን ፤ ቨርጂኒያ ሜሪላንድን እና ከሌሎች የአሜሪካ ግዛቶችም የመጡ ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን ግዙፍ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በዋሽንግተን ሰዓት አቆጣጠር ጠዋት ዘጠኝ ሰዓት ላይ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተጀመረው ወደ አሜሪካ ኮንግረንስም ሄዷል።
ምንም እንኳን መንቻካ ዝናብ ቢዘንብም ሰልፈኛው ሳይበተን የተቃውሞ ድምጹን ሲያሰማ ውሏል።
ሰልፈኞች በኢትዮጵያ የህወሓት መንግስት የሚያደርገውን ግድያ በመቃወም ፤ የአሜሪካ መንግስት ወያኔን መርዳቱን እንዲያቆም እና ይልቁንም በወያኔ እየተቀናበረ ያለውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንዲያስቆም ጠይቀዋል።
ካለፈው ሃምሌ ወር ወደዚህ እንኳን ከ አንድ ሺህ በላይ የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን በወያኔ ሰራዊት መገደላቸው ይታወሳል። ባለፉት ሶስት እና አራት ቀናት የግድያ ቀጠናውን ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ በመውሰድ በኮንሶ አንድን መንደር እንዳለ አረጋውያን እና እመጫት ሴት ጭምር በቤታቸው ውስጥ እያሉ ማንደዱን የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ካሰተላለፈው ዘገባ ለማወቅ ተችሏል።
በጎንደር ከሰው ህይወትም ባለፈ ፤ ቅዳሜ ገበያ በመባል የሚታወቀው ቦታ ሙሉ በሙሉ እንደወደመ ይታወሳል።
ዛሬ በዋሽንግተን ለሰልፍ የወጣው ሰው በ20 ሺዎች ተገምቷል።
የሽፋን ፎቶ : ልደት ሙለታ
ቦርከና
ካነበቡ በኋላ ያጋሩ ፤ ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ!