- Advertisement -
መስከረም 9 2009 ዓ ም
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአማራ ተጋድሎ ጋር የተያያዙ ዜናዎችን በመዘገብ የሚታወቀው ሙሉቀን ተስፋው እንደዘገበው በጎንደር ከተማ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ጎልታ ትታይ የነበረች ወጣት በህወሓት መንግስት ታፍና ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እንደተወሰደች ዘግቧል።
ስሟ ንግስት ይርጋ እንደሚባል የጠቆመው የሙሉቀን ዘገባ ፤ እድሜዋ ገና በሃያዎቹ መጀመሪያ ሲሆን የወያኔ መንግስት ታጣቂዎች ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን አፍኖ ለመውሰድ ወደ ጎንደር በመጡበት ወቅት በተፈጠረው ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ በመምራት እና በማስተባባር ባደረገችው ንቁ ተሳትፎ እንደምትታወቅም ጨምሮ ገልጿል።
ወጣት ንግስት ይርጋ ሃገሯን የምትወድ እና በህዝባዊ እምቢተኝነቱ ንቁ ተሳታፊ ከመሆኗ ሌላ ምንም ወንጀል የሌለባት ሲሆን ፤ ስለ “ጥልቀት ተሃድሶ” ሲያወራ የሰነበተው የወያኔ መንግስት በጎን እየወሰደ ያለው የእብሪት እርምጃ እየደገሰ ያለው ነገር ጠቋሚ እንደሆነ ያሳያል ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡ ሰዎች አሉ።
ቦርከና
ያጋሩ ፤ ቦርከናን በፌስ ቡክ ሼር ያድርጉ