spot_img
Wednesday, March 29, 2023
Homeዜናትምህርት ሚኒስቴር ራስ ደጀን ተራራ በትግራይ ክልል እንደሚገኝ ለአስር ዓመት ያህል በ...

ትምህርት ሚኒስቴር ራስ ደጀን ተራራ በትግራይ ክልል እንደሚገኝ ለአስር ዓመት ያህል በ “ስህተት” በማስተማሩ ይቅርታ ጠየቀ

- Advertisement -

መስከረም 9 2009 ዓ ም

ትምህርት ሚኒስቴር ራስ ደጀን ተራራ በትግራይ ክልል እንደሚገኝ ለአስር ዓመት ያህል በ “ስህተት” በማስተማሩ ይቅርታ ጠየቀ። ከትላንት በስቲያ ይቅርታው የተጠየቀው በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ( አሁን ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን) ነው።

የስድስተኛ ክፍል የእንግሊዝኛ እና የአስረኛ ክፍል የዜግነት እና ግብረገብ ትምህርት የተማሪዎች መማሪያ መጽሃፍት በኢትዮጵያ የሚገኘው ትልቁ የራስ ደጀን ተራራ በትግራይ ውስጥ እንደሚገኝ ሆኖ በመላው ሃገሪቱ ያሉ ተማሪዎች ሲማሩበት ቆይተዋል።

ለአስር አመት ያልታየ ስህተት እንዴት በድንገት በዚህ ሰዓት ሊታይ ቻለ የሚጥቄ የጫረው ዜና ፤ በማህበራዊ ድረ ገጽ ሃሳብ በማካፈል የሚታወቁ ብዙ ኢትዮጵያውያን እንደሚሉት ጉዳዮ አሁን በሃገሪቱ ካለው ቀውስ ጋር ተያይዞ የተነሳ ቢሆንም ፤ ወልቃይት እና ሌሎች የትግራይ ክልል ያልበነሩ የወሎ መሬቶች ጭምር በግልጽ በጉልበት ወደ ትግራይ ተካተው ፤ የራስ ደጀኑ በስህተት ነው መባሉ የሚያሳምን አይደለም ባይ ናቸው። ብዙዎቹ እንደሚሉ የህዝባዊ ወያኔ መንግስት የተስፋፊነት አጀንዳ ከውስጥ ካሰናዳ በኋላ ኢትዮጵያን ሲበትን ለታላቋ ትግራይ ግንባታ ቅድመ ዝግጂት እንደሆነ ያሳያል ይላሉ።

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በአፋር ክልልም አካባቢ የተስፋፊነት አጀንዳ እንዳለው የሚያመላክቱ መረጃዎች አሉ የሚሉ ወገኖች አሉ። በክልሉ በትግራይ ሰዎች ከሚደረጉ መሰረተ ሰፊ የንግድ እንቅስቃሴዎች እስከ ሰፈራ ፕሮግራም ድረስ የሚደረጉ ፕሮግራሞች ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት አለው ባይ ናቸው። በቅርቡ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ከአፋር መሪዎች ስጦታ ተበረከተላቸው የሚል ዜና መውጣቱ ይታወሳል።

በኢሳት በኤርሚያስ ለገሰ እና በመሳይ መካከል በተደረገ ውይይት ወያኔ በኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር የቤንሻንጉል ጉሙዝን እና የጋምቤላን አካባቢች ጨምሮ የትግራይ ክልል እንዳደረገው የሚጠቁም መረጃ (ካርታ ጭምር) ለህዝብ ይፋ አድርገዋል።

ቦርከና
———
ያነበቡትን ያጋሩ ፤ ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
12,460FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here