spot_img
Saturday, May 25, 2024
Homeነፃ አስተያየት" የውስጥ አርበኞቹ እንደሆነ እኔ ቢሮ ድረስ ገብተዋል ። የኔ ራሴ ጽ/ቤት...

” የውስጥ አርበኞቹ እንደሆነ እኔ ቢሮ ድረስ ገብተዋል ። የኔ ራሴ ጽ/ቤት ድረስ ገብተዋል ።አስካለ የምትባለዋ ፀሐፊዬ ለወያኔዎች ሰላይ ነበረች ” ኮሌኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም

ኃይሉ ቢታኒያ
መስከረም 9 2009

ታሪክ የአለፈውን ክስተት የምንማርበት ብቻ ሳይሆን በታሪክ ውስጥ ግለሰቦች እና የተለያዩ ቡድኖች በፈፀሙት ስህተት እና ከውድቀቶቻቸው እኛ ተመሳሳይ ስህተት እንዳንሰራና ተመሳሳይ አወዳደቅ እንዳንወድቅ የምንማርበት እጅግ አስተማሪ ዘርፍ ነው ። የታሪክ ገፆች እንደሚያስነብቡን የአንድ አካባቢ ሰዎች ሰርገው የገቡበት ድርጅት ከመቅፅበት ይፈርሳል ይለናል ።

1~ የቀድሞው የደርግ አባልና የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚደንት የነበረው ፍስሃ ደስታ ከቃልቲ በይቅርታ እንደወጣ ከፍተኛ አቀባበል ያደረገለት አቦይ ስብሃት ነጋ ነበር። የደርጉ ምክትል ሊቀመንበር ፍስሃ ደስታና አቦይ ስብሃት የመጀመሪያ የጉብኝት መርሃ ግብራቸውን አድዋ በመሄድ ንግስት ሳባ ትምህርት ቤት አደረጉ። ለካ የቀድሞው የህውሃት ሊቀመንበር አቦይ ስብሃትና የደርጉ ምክትል ሊቀመንበር ፍስሃ ደስታ የአድዋ ልጆች ብቻ ሳይሆኑ አብሮ አደጎችና የአንድ ት/ቤት የአንድ ዘመን ተማሪዎች ነበሩ። በትግሉ ወቅትም አቦይ ስብሃት አዲስ አበባ ሄዶ የደርግ ኮለኔል ቪላ ቤት ውስጥ ዘበኝነት ተቀጥሮ የስለላ ስራ በሚሰራበት ወቅት ከደርጉ ምክትል ከነበረው ፍስሃ ደስታ ጋር በሚስጢር እየተገናኘ የደርግን የውስጥ ሚስጥር ለህውሃት ያቀብል ነበር።

2~ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት የሆነው አባይ ወልዱና የቀድሞው የህውሃት አባል አዋሎም ወልዱ በረሃ እያሉ ተኽሉ ወልዱ የሚባል የደርግ ባለስልጣን የነበረ ወንድማቸው አዲስ አበባ ውስጥ ይኖር ነበር። የተኽሉ ወልዱ ቤት በአዲስ አበባ የወያኔ ጽህፈት ቤት ነበር። ደርግ «ሞኙ» ከነተኽሉ ወልዱ ጋር አዲስ አበባ ውስጥ ስለ ወንበዴዎች ሲወያይ ይውል የነበረው ነገር ሁሉ አንድም ሳይቀር በበነጋታው ወያኔ እጅ ይገባ እንደነበር አያውቅም ነበር። ከነ ጭራሹም ደርግ ተኽሉ ወልዱ አባይና አዋሎም ወልዱ የሚባሉ ወንድሞች እንዳሉት አያውቅም ነበር። የተኽሉ ወልዱ ቤት ግን ከትግራይ በረሀ የገጠር ልብስ ለብሰው ወደ አዲስ አበባ የሚገተሙ የወያኔ ታጋዮች ምሽግ ነበር።

3~ ሻለቃ ኪሮስ አለማየሁ ፣ ሻለቃ ሲሳይ ሃብቴ ፣ ሻለቃ ሞገስ ወልደ ሚካኤል በደርግ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን የነበራቸው መኮንኖች ነበሩ ። በደርጉ ስብሰባ የተያዘ አጀንዳና ወታደራዊ ሚስጥር ስብሰባው ሳያልቅ ቀድሞ ለወያኔና ለሻአቢያ ይደርሳቸው ነበር ።

ደርግ የወደቀው በወያኔና ሻአቢያ ጦር ተሸንፎ ሳይሆን ከውስጥም ከውጭም ነቀዝ ፣ብል በልቶት ነው።ደርግ ቤቱን ብርግድ አድርጎ ከፍቶ የራሱ ባለስልጣኖች ዘራቸውን ቆጥረው መረጃ ዘመዶቻቸው ለሆኑት ወያኔና ሻአቢያ ይሸጡ ነበር ። ከምእራቡ አለምም ከ CIA ጋር ግጭቱ እየጨመረ ሲመጣ በመጨረሻ ተበታተነ ።

4 ~ ኢህአፓ ~ የአፍሪካ ቦሊሸቪክ እየተባለ የሚጠራውንና እጅግ ጠንካራ የነበረውን ፓርቲ አመድ አድርገው ያፈራረሱት ዘሩ ክህሽን ፣ እያሱ አለማየሁ ፣ ዮሴፍ አዳነ የአንድ መንደር ልጆች ናቸው። እነ ጌታቸው ማሩን የመሰሉ ብሩህ አእምሮ ያላቸውን ልጆች ፊታቸው ላይ አሲድ ደፍተው በአጭር ያስቀሯቸው እነዚህ እፉኝቶች ናቸው ። እነ ቲቶ ህሩይንና አክሊሉ ህሩይን የመሰሉ በመቶ ሺህዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶች ፍጅት ተጠያቂዎቹ እነ ዘርኡ ክህሽን ናቸው።

5 ~ ኢደፓ የተባለውን ድርጅት ለወያኔ ገፀ በረከት ያቀረበው ከሃድው ልደቱ አያሌው ይመስላችኋልን? ። ልክ ናችሁም ልክ አይደላችሁምም ። እርግጥ ልደቱ አያሌው ከወያኔ ጋር በመሞዳሞድ ቅንጅት የተባለውን ፓርቲ ሊያፈራርስ ችሏል። ከዛ በፊት ግን ኢደፓ ፓርቲ ውስጥ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል በመሆንና እነ ልደቱ አያሌውን ከደህንነት ጋር በማደራደር ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ፌስቡክ የምታውቁት ዳንኤል ብርሃኔ ነው። ዳንኤል ብርሃነ የኢደፓ ከፍተኛ አመራር የነበረና ኢደፓን አዳክሞ” ከእጅ አይሻል ዶማ ” ያደረገ ሰው ነው።

6~ ግንቦት 7 ~ ግንቦት ሰባት ከትህዴን ጋር በተቀላቀለ ማግስት ሞላ አስገዶም ያደረገውን ክህደት ለእናንተ መናገር ለቀባሪው ማርዳት ነው ።

7~ አንድነት ~ አንድነት የሚባለው የፖለቲካ ፓርቲ እጅግ ጠንካራ የተባለ የፖለቲካ ፓርቲ ነበር ። ድርጅታዊ ስራውንም የውስጥ ሚስጥሩን ጠብቅ ለጠላት በሩን ሳይከፍት ሲሰራ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን የአረና ከፍተኛ አባል የነበረ አስራት አብርሃም የተባለ የአንድነትን ለምድ የለበሰ ተኩላ አንድነት ፓርቲ ቢሮ ውስጥ ተገኝቶ በአባልነት ተመዘገበ ። ወር ሳይቆይ የአንድነት ፓርቲ ሚስጥር ለደህንነት መድረስ ጀመረ ። ብጥብጥ ተጀመረ ። ፀጉረ ልውጡ ጆሮ ጠቢ አንድነትን በተቀላቀለ በወር ውስጥ አንድነት ፓርቲ ስርአተ ቀብሩ ተፈፀመ ። …

አሁንስ ሁሉንም መጥቀሱ ደከመኝ ሌሎችም እጅግ ብዙ ምሳሌዎች ነበሩ ። ለማንኛውም ፈረንጅ ” ረጅም ጉዞ የምትጓዝ ከሆነ አብሮህ የሚጓዘውን ጓደኛህን በጥንቃቄ ምረጥ ” ይላል። ይሄ የሚናቅ ምክር አይመስለኝም።

በአሉ ግርማ የፃፈው መፅሃፍ ላይ አንድ ገፀ ባህሪ አለው “ሻለቃ ታደሰ ቆሪቾ ” የሚባል ። ስለ ሻለቃ ታፈሰ ቆሪቾ አሁን እዚህ አልፅፍም ከፈለጋችሁ መፅሃፉን አንብቡ ። በአሉ ግርማ ግን በኦሮማይ መፅሃፉ ደርግን ወሳኝ መረጃ በመስጠት ምክር ቢጤ መክሮት ነበር ።እንደ እነ ሻለቃ ታደሰ ቆሪቾ ከእነ ስእላይ በርሄ ጋር በመሆን እየቦረቦሩህ ነውና ተጠንቀቅ ቢለው ደርግ ሞኙ በአሉ ግርማን ገደለው።

_____
ያነበቡትን ያጋሩ ፤ ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ

ማስታወቂያ
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here