መስከረም 10 2009 ዓ ም

ምንጭ : oromia-parliamentarians
የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራዊያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ሊቀመንበር እና የክልሉ ፕሬዝዳንት ሙክታር ከድር እና የፌደራል መንግስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ወ/ሮ አስቴር ማሞ ራሳቸውን በፈቃዳቸው ከስልጣን እንዳገለሉ የገዥው የህወሓት ቡድን አፈቀላጤ እንደሆነ የሚነገርለት ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል።
ራሳቸውን በኃላፊነት ያገለሉት አንድ ሳምንት ፈጀ ከተባለ “ጥልቅ የተሃድሶ” አጀንዳ ከያዘ የፖርቲ ግምገማ በኋላ እንደሆነ ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።
በምትካቸው ለማ መገርሳ ሊቀመንበር ፤ ወርቅነህ ገበየሁ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው እንደተመረጡም ታውቋል።
በመላው ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የህወሓት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እና በፋና ብሮድካስቲንግ በኩል በተከታታይ በመቅረብ ስለ “ጥልቅ ተሃድሶ“ እንዳወሩ እና ተሃድሶው ሙስናን በሙስና ላይ እንደሚዘመት እና ባለስልጣናትን ማባረር እንደሚጀመር ፍንጭ እንደሰጡ ይታወሳል። ከዚያ አንጻር እና እስከዛሬ እንደሚታወቀው ህወሓት በኢሃዴግ አባል ድርጂቶች ላይ ባለው የፈላጭ ቆራጭነት ሚና አኳያ ኦህዴድ ውስጥ የተፈጠረው ለውጥ በኦህዴድ ተነሳሺነት የመጣ እና ከሙስና ጋር የተያያዘ ነው ብሎ ለማስብ ያስቸግራል።
ብአዴን እና ደቡብ ህዝቦች ድርጂትም ተመሳሳይ “በጥልቀት የመታደስ” አጀንዳ መሰረት አድርገው ግምገማ በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል ፤ ምናልባትም ተመሳሳይ ነገር ይጠበቃል።
ቦርከና
ያነበቡትን ያጋሩ ፤ ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ማድረግ አይርሱ