አጂሬ ባሻ
መስከረም 13 2009 ዓ ም
ዛሬ ደሞ አብርሃ አማራ በአማራነቱ መደራጀቱ በህውሃት የመሸነፉ ምልክት ነው ይለናል ምክንያቱ ደሞ ከኢትዮጵያዊነት መውረድ አልነበረበትም ነው እንግዲህ አብርሃ እርሱ እራሱ የትግራይ ብሄርተኛ ከሆነው አረና ትግራይ ውስጥ ቁጭብሎ በመስኮት ሲያስተውል የአማራ መደራጀት በህውሃት መሸነፍ እንደሆነ ተገልጦለት ይህን ምክር ሲመክረን ግን እርሱ ሲደራጅ እውነት እኛ ስንደራጅ እብደት የሚሆንበት ምክንያት ባስበው ባስበው አልገባህ አለኝ እርሱም ሊነገረን አልቻለም የቅርብ ወዳጆቼ ጭምር በአብርሃ ላይ በያዝኩት አቊም ሲተቹኝ መልሼ እራሴን ለማየት ሞክሬ ነበር ግን ትክክል ነኝ እስኪ የአብርሃን የሰሞኑን ምክሩን እንኲ በቀላሉ እንፈትሸው
አብርሃ እና ወልቃይት ጉዳይ
አብርሃ የዚህ የወልቃይት ጉዳይ እንዲህ ከምፈንዳቱ በፊትም ሆነ አሁን የትግራዋይ ተቃዋሚ(የ አረና ህዝብ ግንኙነት መሆኑን ልብ ይሏል) ስለሆነ በአመዛኙ ከሚኖርበት የትግራይ ክልል አንፃር ውሃ ሚቊጥሩ ትችቶችን በህውሃት ላይ ይሰነዝር ስለነበር በደንብ እከታተለው ነበር ይሁን እና ከወልቃይት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ግን በጣም የቂል የሚመስሉ መከራከርያወችን ይዞ መጥቷል ከነዚም አንዱ እንደሚከተለው ነው
“የኩናማ ጉዳይ ነው ምክንያቱም ኩናማ የኩናማ ስለሆነ የወልቃይትም ጉዳይ የወልቃይት ነው ምክንያቱም ወልቃይት የወልቃይት ስለሆነ” ይለናል ከዚያም ቀጠል አርጎ መሬቱ የትም ቢሆን የኢትዮጵያ እንደሆነ ይደመድማል ። እዚህ ጋር ሁለቱን ነጥቦች አንድ በአንድ ለማየት እንሞክር እስኪ
“የኩናማ ነገር የኩናማ ነው ” ትክክል ነው ልቀበል ምክያቱም ኩናማ እራሱን የቻለ ብሄር በመሆኑ
እኔን ያልገባኝ ግን ” የወልቃይት ጉዳይ የወልቃይት የወልቃይት ነው ” የሚለው ነው ::
የወልቃይት ጥያቄ የአማራነት ጥያቄ መሆኑን ሆንብሎ ዘሎታል እዚህ ጋር አብርሃ ከአባይ ወልዱ የሚለየው ትንሽ የጅል ብልጥ ልሁን ማለቱ እና እንደ እነ እባይ ትጨፈጨፋላቹ ብሎ በአደበባባይ አለመዛቱ ብቻ ነው
አብርሃ እና የአንድነት ትርክቱ
እንግዲህ አብርሃ አረና ትግራይ የሚባል የብሄር ድርጅት ውስጥ ቁጭ ብሎ የአንድነት አቀንቃኝ ሆኖ ከተፍ ይል እና የወልቃይት መሬት ችግር የለውም የትም(ትግራይ) ቢሆን የኢትዮጵያ ነው ብሎ ኢትዮጵያዊነትን ከሰበከን በኊላ በቅርቡ የደህንነት ቢሮ የትግራይ ተወላጆች የዘር ፍጅት ደረስባቸው የሚል ድራማ በሰራ ጊዜ የኢትዮጵያን አንድነት ያስከበረውን (የአንድነት ሃሌሎች ሙሉ በ ሙሉ ሚስማሙበት እንደሆነ ይሰመርልኝ) ሚኒሊክን አራጅ ብሎ ማለቱ ፣ የሃውዜንን ጭፍጨፋ ሙሉ ለሙሉ ለደርግ መስጠቱ ለሽፋንም ቢሆን ያነሳውን የአንድነት መከራከርያ አፈር ያበላዋል በዛ ላይ ይህንን ምክር የሚመክረን አረናውስጥ ሆና ከመሆኑ ጋር ገምደን ስናየው የአብርሃ የቃላት እና የስትራቴጂ አክሮባት ይገለፅልናል
አማራ እና ኢትዮጵያዊነት
ከአሁን በፊት በነበረችው ኢትዮጵያ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ማንነት የሚባለው አማራነት የተጫነው እና የአማራ የበላይነት እንዳለ ከወያኔ በኃላ የወጡ በእንድም ሆነ በሌላመንገድ ከስርአቱ የሚቀዱት ድርሳናት ያትታሉ። የእነዚህ ድርሳናት የያዙት ትርክት እውነትም ይሁን ሃሰት ላለፉት ሃያ አምስት አመታት አማራው ላይ ካደረሱት የስነልቦና ተፅእኖ በላይ እንደ ዜጋ የመኖር ህልውናውን ጥያቄ ውሥጥ ከትቶት ቆይቷል።
ለምሳሌ ከቤንሻንጉል እና ከጉራፈርዳ በህውሃት ቀጥተኛ ተፅእኖ የተፈናቀሉትን አማሮች እንዲሁም የበዶናውን ጭፍጨፋ ልብ ይሏል ከዚህ የተሳሳተ የኢትዮጵያዊነት አረዳድ ጋር ተያይዞ (ባለፉት ነገስታት የብሄር ማንነት ላይ ትልቅ ጥያቄ ተያይዞ) አማራ እንደብሄር ተቃሚ አልነበረም።በሳሳተው ትርክት ግን የገፈቱ ቀማሽ ሆኗል። ከዚህ አንር አማራው ለሃያ አምስት አመታት ያረፈበትን የግፍ አርጩሜ ማጠፍ የሚችለው እንደህዝብ ሲደራጅ ነው ከዚህም አልፎ አማራው ለዚች ሃገር የከፈለውን ዋጋ ይበቃል። ኢትዮጵያ በአዲስ ቅርጵ እንድትመሰረት ማስገደድ ይችላል።
እንደ መውጫ
አሁን ባለው ወቅታዊ የፓለቲካ አየር ንብረት ብሄር ተኮር ፌደራሊዝሙ ኢ-ተቀልባሽ እንደሆነ እሙን ነው ከዚህ አንፃር አማራው እንደ ህዝብ ሆንተብሎ ህልውናውን ጥያቄውስጥ የሚከት አደጋ የተጋረጠበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እንደህዝብ ለመቀጠል የአማራ ብሄርተኝነት በእጅጉ አንገብጋቢ እና የ ኦክስጅን ያህል አስፈላጊ ነው። ከዚህ አንፃር አብርሃን እና ከመሰሎቹን ለምክራቸው እያመሰገንን በያለንበት ያአማራን ብሄርተኝነት ማፋፋም ለ ነገ የማንለው ጊዜው የጣለብን ግዴታችን ነው። ይህ ትግል የመላው አማራ ትግል ነው
አማራነትን የምትቀበል ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
#አማራ ይደራጃል _አማራ ያሸንፋል