spot_img
Monday, December 4, 2023
Homeዜናበኦሮሚያ ምስራቅ አርሲ አራት የአጋዚ ክ/ጦር አባላት መገደላቸው ተገለጸ (ኢሳት)

በኦሮሚያ ምስራቅ አርሲ አራት የአጋዚ ክ/ጦር አባላት መገደላቸው ተገለጸ (ኢሳት)

advertisement

ኢሳት
መስከረም 13 ፥ 2009

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ አርሲ ዞን ዛሬ አርብ እለት አራት የአጋዚ ክ/ጦር አባላት መገደላቸው ታወቀ። አንደኛው ደግሞ መማረኩን የአይን ምስክሮች በምስል አስደግፈው ለኢሳት አድርሰዋል። የተማረከው የሰራዊት አባል ለማስለቀቅ በሚል ተጨማሪ ሃይል ወደ ስፍራው መድረሱና ተኩስ መቀጠሉን ለመረዳት ተችሏል።

በምስራቅ አርሲ አጄ አካባቢ ልዩ ስሙ ቀሲሳ ተራራ በተባለ አካባቢ በህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል በሚል በአጋዚ ክፍለ ጦር አባላት ላይ ጥቃት የፈጸሙት የአካባቢ ነዋሪዎች መሳሪያዎቹን ነጥቀው መሰወራቸው ታውቋል።

በስርዓቱ ይፈጸማል ያሉትን ግፍና በደል በመቃወም፣ በተለይም በህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመግታት በሚል ሰራዊቱ አባላት ላይ ዕርምጃ የወሰዱት ግለሰቦች ትጥቅ ይዘው ለትግል መነሳታቸውንም በቪዲዮ ባሰራጩት መግለጫ አስታውቀዋል።

በኦሮሞ ህዝብና በሙስሊሙ ላይ የሚደርሰው ጥቃት መቀጠሉ እንዳስቆጣቸውም ተደምጠዋል።

ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አራት አጋዚ ክ/ጦር አባላት መገደል እንዲሁም የአንደኛው መማረክ የተረጋገጠ ሲሆን፣ በስፍራው ከተኩሱ ጋር ተያይዞ ስለደረሰው ጉዳት የታወቀ ነገር የለም። የተማረከው ወታደር እንዳልተለቀቀ ታውቋል።

- Advertisement -Early Bird Holiday Deals! Before you know it, the holidays will be right around the corner! Take advantage of our early bird deals today and save up to $40 on our fees with code SPOT40!
Stay Connected
28,789FansLike
13,920FollowersFollow
8,540SubscribersSubscribe
Stacy Adams
Must Read
Related News

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here